ለውረን አሽሊ ዳይጎል (ላቲን፡ Lauren Ashley Daigle) (የተወለዱት እ.ኤ.አ መስከረም 9፣ 1991 ዓ.ም ነው)[1][2] የአሜሪካ ዘመናዊ የክርስቲያን ሙዚቃ ዘማሪና እና የዜማ ደራሲ ናቸው። ወደ ሴንትሪሲቲ ሙዚቃ ከተሰየሙ በኋላ "ኻው ከን ኢት ብ" የተባለውን የመጀመሪያ አልበማቸውን እ.ኤ.አ በ2015 አወጡ። መዝሙሩም በቢልቦርድ ከፍተኛ የክርስቲያን አልበሞች ገበታ ላይ ቁጥር 1 ሆኗል፣ በአር.አይ.ኤ.ኤ(RIAA) ፕላቲነም የምስክር ወረቀት ያስገኘ ሲሆን ክርስቲያናዊ ኤርፕለይ ቢልቦርድ ገበታ ላይ የመጀመሪያ የሆኑትን ሌሎች ነጠላ ዜማዎችንም አፍርቷል፤ እነርሱም ፌርስት፣ ትረስት ኢን ዩ እና ኦ ሎርድ ናቸው።
የዳይጎል ሦስተኛው የስቱዲዮ አልበም የሆነው “ሉክ አፕ” በመስከረም ወር 2018 ተለቋል። ይህም “ዩ ሰይ” በሚለው ነጠላ ዜማ የፖፕ ክሮስ-ኦቨር ስኬት አመጣና በቢልቦርዱ 200 ዝርዝር ውስጥ ሦስተኛ ሊሆን ቻለ። በተጨማሪም ከ 20 ዓመት በላይ ሴቶች ምድብ በብዛት የተሸጠ የክርስቲያን አልበም የተባለ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ወደ 115 ሺህ የሚጠጋ ጊዜ በመሸጥ በብዛት የተሸጠ የክርስቲያን አልበም ለመሆንም በቅቷል። [3] የአልበሙ መሪ ነጠላ ዜማ የሆነው "ዩ ሰይ" በብዛት የተሸጠ በሚል በቢልቦርድ 100 ስር 29ኛ ደረጃ የያዘ ሲሆን ለ101 ሳምንታት በቢልቦርድ "ሆት ክርስቲያን ሶንግ" ቻርት ላይ አንደኛነቱን አስጠብቋል። አልበሙና ነጠላ ዜማው ዳይጎልን ለግራሚ አዋርድስ አብቅቷቸዋል።
ዳይጎል የተወለዱት በሌክ ቻርልስ ሉዊዚያና ውስጥ ሲሆን እድገታቸው ደግሞ የሉዊዚያና ግዛት ላፋዬቴ ነው። በአካባቢያቸው ዚዴኮ ፣ ብሉዝ እና ካጁን ሙዚቃ ተጽዕኖ አድርጎባቸዋል።[4][5] ሁለ ከመዘመራቸው የተነሳ እናታቸው የሙዚቃ ሳጥን ይሏቸው ነበር።[6][7]