ሩት ነጋ (ላቲን፡ Ruth Negga) (የተወለዱት እ.ኤ.አ. ጥር 7 ቀን 1982 ዓ.ም.) ኢትዮ-አይሪሽ ዘግነት ያላቸው ተዋናይ ሲሆኑ በደምብ የታወቁት በኤ.ኤም.ሲ (አፍርካና መካከለኛው ምሥራቅ የቴሌቪዥን ጣቢያ) በቀረቡት ፕሪቸር እና ላቪንግ በተሰኙ የፊልም ሥራቸው ነው።[1]
ሩት በካፕታል ሌተር(2004)፣ ዓይሶለሽን(2005)፣ ብረክፋስት ኢን ፕሉቶ(2005) እና ዋር ክራፍት(2016) በተባሉ ፊልሞች ውስጥ ታይተዋል።[2] ሌሎች የቴሌቪዥን ፕሮጀክቶች የቢ.ቢ.ሲ. ሚኒ ስይረስ ክሪምናል ጃስትስ ፣ የአር.ት.ኢ ላቭ/ኼት፣ የኤ.ቢ.ሲ. ማሪቭሌስሲ ኤጀንት ኦቭ ኤስ.ኤች.አይ.ኤል.ዲ ተሳትፈዋል። ሩት በፕሪቸር(2016) እንደ ቱሊፕ ኦኻሬ ሆኖ የመሪ ተዋናይ ገጸባሕሪ ተጫውተዋል።