1 ሪም-ሲን ከ1734 እስከ 1675 ዓክልበ. (ኡልትራ አጭሩ አቆጣጠር) የላርሳ መጨረሻ ንጉሥ ነበረ።
ሪም-ሲን በ1734 ዓክልበ. ወንድሙን ዋራድ-ሲንን በላርሳ ዙፋን ተከተለው። አባቱ ኤላማዊው-አሞራዊው አለቃ ኩዱር-ማቡግ ነበር።
በ1721 ዓክልበ. ጎረቤቶቹ ባቢሎን፣ ኡሩክ፣ ራፒቁምና ኢሲን ላርሳን ለመቃወም በውል ተባበሩ። ሪም-ሲን ግን ሁላቸውን በአንድ ውግያ አሸነፋቸውና መንግሥቱን ያስፋፋ ጀመረ። በ1714 ዓክልበ. ኡሩክን ዘረፈ። በ1712 ግን የባቢሎን ንጉስ ሲን-ሙባሊት ድል አደረገው። በ1710 ዓክልበ. የኢሲንን ግዛት ወረረው፣ በ1705 ኢሲንን ከመጨረሻ ንጉሱ ከዳሚቅ-ኢሊሹ ያዘ። ይህም በሪም-ሲን መንግሥት በ30ኛው አመት ሆነ። ከዚህ ዓመት ጀምሮ የላርሳ ዓመታት ከኢሲን ውድቀት ጀምሮ ተቆጠሩ፤ ይህም አቆጣጠር እስከ ሪም-ሲን ዘመን መጨረሻ እስከ 1675 ዓክልበ. (= «31 ዓመት ኢሲን ከወደቀ») ተጠቀመ።
በ1699 የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ኢሲንንና ኡሩክን ከሪም-ሲን ያዘ። (ሆኖም የላርሳ ዓመት ከኢሲን ውድቀት መቆጠር ያንጊዜ አልተወም።) በመጨረሻ በ1675 ዓክልበ. ሃሙራቢ ላርሳን ከበበው፤ ከ6 ወር በኋላ ላርሳ ለባቢሎን ወደቀ።[1]ይህም በሪም-ሲን 60ኛው ዘመነ መንግሥት ሆነ።
ቀዳሚው ዋራድ-ሲን |
የላርሳ ንጉሥ 1734-1675 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ የለም (ሃሙራቢ ላርሳን ያዘ።) |