የነሐሴ ቀናት | ||||||
1 | 2 | 3 | 4 | 5 | 6 | 7 |
8 | 9 | 10 | 11 | 12 | 13 | 14 |
15 | 16 | 17 | 18 | 19 | 20 | 21 |
22 | 23 | 24 | 25 | 26 | 27 | 28 |
29 | 30 |
ነሐሴ የወር ስም ሆኖ በሐምሌ እና በጳጉሜ ወራት መኻል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ አሥራ ሁለተኛው (፲፪ ኛው) የወር ስም ነው። «ነሐሴ» ከግዕዙ «ነሐሰ» ከሚለው ቃል የመጣ ነው።[1] ነሐሴ የክረምት ሦስተኛው ወር ነው።
በዘመን ቆጠራ ቀለበት ውስጥ ተውሳኳን 'የጳጉሜ ወርኅ' ለመሻገር ጉጉቱ ያይላል፤ መስከረም እስኪጠባ። መስከረም የወራት ሁሉ ቁንጮ ነውና። መስከረም ዘመን ያስረጃል፤ አዲስ ሕይወትና ተስፋ ደግሞ ይደግሳል። ደራሲ ካህሳይ ገብረ እግዚአብሔር "ቀዳማይ፣ ርዕሰ ክራሞት፣ መቅድመ አውርኅ፣ ርዕሰ ዐውደ ዓመት፣ የክረምት ጫፍ መካተቻ፣ የመፀው መባቻ" ይሉታል ወርኃ መስከረምን። የኢትዮጵያያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የባህር ሐሳብ ሊቃውንት መስከረም 1 ቀን ዓለም የተፈጠረበት፤ ኖኅ ከጥፋት ውኃ በኋላ ውሃው መጉደሉን ለማረጋገጥ ወደ ምድር የላካት እርግብ ቅጠል ይዛ የተመለሰችበት፣ እስራኤላዊያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ ቀይ ባሕርን የተሻገሩበት የብስራት ዕለት እንደሆነ ያነሳሉ። በእነዚና ሌሎች ኃይማኖታዊ ትውፊቶች ከጥንት ጀምሮ ነው መስከረም ለዘመን መለወጫነት የተመረጠው ይላሉ። ዕለቱም 'ርዕሰ ዓውደ ዓመት' ይሉታል። መስከረም ለመልክዓ ምድሩ፣ ለሰውና ለእንስሳት ሁሉ 'ፍስኃ ወተድላ' በማለት የደስታና የተድላ ወር መሆኑን አበው ይገልጻሉ። በመስከረም ምድር ትረጋለች፣ በአበቦች ታጌጣለች፣ በእንቁጣጣሽ ትፈካለች። ውኆች ይጠራሉ። በሰማዩ ሰማያዊ ላይ ብርሃን ይወጣል፤ የጥቁር ደመና ጋቢ ይገፈፋል፤ ክዋክብት በሰማይ ብረት ምጣድ ላይ መፈንጨት ይጀምራሉ። እጽዋትና አዝዕርት እንቡጦች ይፈነዳሉ። የመብረቅ ነጎድጓድ ተወግዶ የሰላምና የሲሳይ ዝናብ ይዘንባል። እንስሳት የጠራ ውሃ እየጠጡ፣ ለምለም ሳር እየነቸረፉ ይቦርቃሉ። እርሻ የከረሙ በሬዎች፣ ጭነት የከረሙ አህዮች መስከረም አንጻራዊ የእፎይታ ወርኃቸው ነው። ነጎድጓድ በአዕዋፋት ዝማሬ ይተካል። ንቦች አበባ ይቀስማሉ፤ ቀፏቸውን ያደራሉ። ቢራቢሮ ሳትቀር 'በመስከረም ብራ ከኔ በላይ ላሳር' ብላ ትከንፋለች። ለሰው ልጆች የመስከረም ደጅ ሲከፈት ግብዣው የትየሌለለ ነው። ምድር ብቻ አይደለችም በ’እንቁጣጣሽ’ የምትዋበው። መስከረም የሰው ልጆችም በተለይም ለወጣቶች የፍቅር፣ የእሸትና የአበባ ወር ነው። የሰላም፣ የንጹህ አየር፣ የጤና ድባብ ያረብብበታል። የጋመ በቆሎ እሸት ጥብስ፤ ቅቤ ልውስ፤ ቅቤ በረካ፤ መስቀል፣ ደመራ ይናፈቃል። የተጥፋፋ ይገናኛል። 'ሰኔ መጣና ነጣጠለን' ብለው ወርኃ ሰኔን የረገሙ ተማሪዎች ተናፋቂያቸውን ያገኛሉና 'መስከረም ለምለም' ብለው ያሞካሹታል። የገበሬው የሰብል ቡቃያ ያብባል፣ እሸት ያሽታል። ጉዝጓዝ ሣር፤ ትኩስ ቡና ይሸታል። 'መስከረም ሲጠባ ወደ አገሬ ልግባ …' እንዲሉ የተሰደዱት በአዲስ ዓመት መባቻ የአገራቸውን አፈር ያማትራሉ። የተጥፋፋ ይገናኛል። ’ኢዮሃ አበባዬ፤ መስከረም ጠባዬ’ የሚሉ ሕጻናት ተስፋና ምኞታቸውን በወረቀት ያቀልማሉ፤ የአበባ ስዕላት ይዘው በየደጃፉ ይሯሯጣሉ፣ የ’እደጉ’ ምርቃት ያገኛሉ፤ በደስታ ይንቦጫረቃሉ።
አየለ ያረጋል /ኢዜአ/:-
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |