ኤሪዱ (ወይም ኤሪዱግ / ኡሩዱግ፣ ከሱመርኛ ኤሪ-ዱጋ «ጥሩ ከተማ») ከዑር ወደ ደቡብ-ምዕራብ 7 ማይል የራቀ ጥንታዊ ከተማ ነበረ። በሱመር በመስጴጦምያ በመስጊዶች ዙሪያ ከተመሠረቱት ከተሞች አንዱ ሲሆን ከሁላቸው ወደ ደቡብ ተገኘች።
በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ ኤሪዱ የዓለሙ መጀመርያ ከተማ ነበረ። እንዲህ ሲል፦
በሱመር አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ከማየ አይህ ቀድሞ ከተሠሩት 5ቱ ከተሞች አንዱ እንደ ነበር ተባለ። ለመሆኑ በሥነ-ቅርስ ረገድ የሱመር መጀመርያ ከተማ ሆኖ ይመስላል። ሲገነባ ኤፍራጥስ ወንዝ ወደ ፋርስ ባሕር ወሽመጥ ወደብ በሚፈስስበት ስፍራ እንደሆነ ቢታሥብም ዛሬ ግን በአሸዋ ጥርቅም ምክንያት ባሕሩ ከቦታው በጣም ይርቃል።
የኤንኪ (አምላክ ወይም ጣኦት) ቤተ መቅደስ በኤሪዱ 'ኤ-አብዙ' ተባለ። የኤንኪ ሚስት የኒንሁርሳግ ቤተ መቅደስ 'ኤ-ሳጊላ' ደግሞ በአካባቢው ነበረ።
መምህርዋ ኬት ፊልደን እንደምትለው፣ «ከ2050 ክ.በ. ገዳማ በፊት ከተማው ዝቅ ብሎ መኖርያ እንደሆነ ትንሽ ምልክት ብቻ አለ። ንጉስ አማር-ሲን (2055-2047 ክ.በ. ገዳማ) ካልጨረሰው መስጊድ በታች 18 የጡብ ቤተ መቅደሶች አሉ።»
በኋላ ዘመን በአሦር ቤተ መንግሥት ልዩ ህኪሞች ስለ በሽታ ጠንቆች ህክምና ለማወቅ የኤሪዱ ጥንታዊ ጥበብ መማር ነበረባቸው።
በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር በኩል፣ ኤሪዱ የመጀመርያ ነገሥታት ከተማ ተብሎ እንዲህ ይቀጥላል፦
(የነገሥታት ዝርዝሩ ከጥፋት ውኃ በፊት ለገዙት ነገሥታት እጅግ ረጅም ዘመን ይሰጣቸዋል።)
ስለ ኢናና (የኡሩክ ከተማ ሴት አምላክ) ደግሞ አንዳንድ ትውፊት ይተረክ ነበር። የሥልጣኔ ስጦታ ለመቀበል ወደ ኤሪዱ መጓዝ እንደ ነበረባት ተባለ። ኤንኪ በመጀመርያ የሥልጣኑን ምንጭ ለመመለስ ቢሞክርም፣ ኋላ ግን ኡሩክ የአገሩ መሃል መሆኑ ተስማማው።
አንዳንድ የባቢሎን ጽሕፈት ደግሞ አምላካቸው ማርዱክ ኤሪዱን እንደ 'መጀመርያ ቅዱስ ከተማና የአማልክት መኖርያ' ሆኖ እንደ ፈጠረው ይላል።
የመምህር ዴቪድ ሮህል ኅልዮ በጣም ትኩረት ይስባል። በሱ አሳብ ዘንድ፣ ኤሪዱ ከዑር ወደ ደቡብ መጀመርያይቱ ባቢሎን ነበረችና የባቢሎን ግንብ ሥፍራ በኋለኛው ባቢሎን ሳይሆን እዚህ እንደተገኘ ያምናል። ምክንያቶቹም፦
«ባቢሎን» (ባብ-ኢሊ) ማለት የኤሪዱ መጠሪያ እንደ ነበር የሚል ማስረጃ በሌሎችም ጥናቶች አለ።[1]