እሽቢ-ኤራ ከ1900 እስከ 1872 ዓክልበ. ግድም ድረስ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) የኢሲን ንጉሥና ከ1878 በኋላ የሱመር ንጉሥ ነበር።
በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ላይ ለ፴፫ ዓመታት እንደ ገዛ ሲለን፣ ከ፳፱ ወይም ፴ የዓመት ስሞች ብቻ ለእርሱ ተገኝተዋል። ከነዚህም ውስጥ ለምሳሌ፦[1]
በኡር ንጉሥ ኢቢ-ሲን ዘመን (1901-1879 ዓክልበ.) የዑር መንግሥት ኃይል እየወደቀ ነበር። ጠላቶቹ አሞራውያንና ኤላም ያስቸግሩት ጀመር። በዚያም ዓመት ታላቅ ረሃብ በመካከለኛ ምሥራቅ ጀመረ። ኢሽቢ-ኤራ አንድ አሞራዊ ሹም ከማሪ ሲሆን ኢቢ-ሲን የኒፑርና የኢሲን ገዥ አደረገው። በረሃብ ምክንያት እህል ለዑር ለመግዛት ኢቢ-ሲን ብዙ ብር ለኢሽቢ-ኤራ ሰጠው። ኢሽቢ-ኤራ ግን የኢሲን መንግሥት ነጻነት አዋጀ። ኤላማውያን ሲያስቸግሩ ኢሽቢ-ኤራና ኢቢ-ሲን ይዋጋቸው ነበር። በመጨረሻ በ1879 ዓክልበ. ግድም ኤላማውያን በንጉሣቸው ኪንዳቱ ሥር ዑርን አጠፉ። በሚከተለው ዓመት አሞራዊው እሽቢ-ኤራ ኤላማውያንን ከዑር አስወጣቸውና የሱመርና አካድ ላዕላይነት ያዘ።
ቀዳሚው የኡር ንጉሥ ኢቢ-ሲን |
የሱመር ንጉሥ 1878-1872 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሹ-ኢሊሹ |
ቀዳሚው የለም |
የኢሲን ንጉሥ 1900-1872 ዓክልበ. ግድም |