República do Acre |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
|
||||||
የአክሬ ክፍላገር ሥፍራ
|
||||||
ዋና ከተማ | አንቲማሪ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ፖርቱጊዝኛ፣ እስፓንኛ | |||||
መንግሥት {{{ |
|
|||||
ዋና ቀናት 1891 ዓ.ም. 1896 ዓ.ም. |
ምስረታ መጨረሻ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) |
191,000 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ1892 ግምት |
10,000 |
የአክሬ ረፐብሊክ (ፖርቱጊዝኛ፦ República do Acre), ( እስፓንኛ፦ República del Acre) ወይም የአክሬ ነፃ መንግሥት (ፖርቱጊዝኛ፦ Estado Independente do Acre), (እስፓንኛ፦ Estado Independiente del Acre) የዛኔ የቦሊቪያ ግዛት በነበረችው በአክሬ ክፍላገር ውስጥ የታወጁት ሦስት ተከታታይ ተገንጣይ መንግሥታት ነበሩ። እነዚህም ሦስቱ ተገንጣይ መንግሥታት ከ1891 እስከ 1896 ዓ.ም ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ የቆሙት ናቸው። በ1896 ዓ.ም. ክፍላገሩ በይፋ ወደ ብራዚል ተጨመረችና እሳካሁን የብራዚል አክሬ ክፍላገር ትባላለች።
ከ1850 ዓም ያህል ጀምሮ፣ ክፍላገሩ በጎማ ኢንዱስትሪ ማዳበሩ ምክንያት በ፵ ዓመታት ውስጥ በብራዚል ዜጎች ተሞልቶ ነበር።[1] በ1860 ዓም የአያቹኮ ስምምነት ክፍላገሪቱ የቦሊቪያ ግዛት መሆንዋን አረጋግጦ ነበር።
ከ1881 ጀምሮ ፖርቱጊዝኛ ተናጋሪዎች የሆኑት የብራዚል ሰዎች የአክሬ ኗሪዎች ብዛት ሆነው፣ ከቦሊቪያ ለመገንጠልና ትንሽ ጊዜ ሳያልፍ ወደ ብራዚል እንዲጨመር የሚለውን ዕቅድ ያሥቡ ጀመር። በ1891 ዓም ሉዊስ ጋልቬዝ ሮድሪጌዝ ደ አሪያስ እሱም የእስፓንያ ዜጋና ጋዜጠኛ ሲሆን አንድ ሠልፍ በዘመቻ ከብራዚል ወደ አክሬ መራ እና በሐምሌ 1891 ዓም «የአክሬ ሪፐብሊክ» ፕሬዚዳንት መሆኑን በአዋጅ አሳወቀ። ሪፐብሊኩን በቅርቡ ከብራዚል ጋራ ለማዋሐድ ያሠበው ቢሆንም፣ በሚከተለው መጋቢት 1892 ዓም ግን የብራዚል መንግሥት ሥራዊቱን ልኮ ጋልቬዝን አሠረና ክፍላገሪቱን ወደ ቦሊቪያ ሥልጣን መለሡዋት። ጋልቬዝ ወደ እስፓንያ በስደት ተመለሠና ለግዜው የአክሬ ኗሪዎች ከቦሊቪያም ሆነ ከብራዚል መንግሥታት መቃወም ያገኙ ነበር።
በኅዳር 1893 ዓም ሁለተኛ ሞክረው የአክሬ ኗሪዎች ሁለተኛ «የአክሬ ሪፐብሊክ» አዋጁ፤ ሮድሪጎ ደ ካርቫዮ ፕሬዚደንት ተደረገ። ሆኖም እንቅስቃሴው ዳግመኛ ስለ ተቃወመ ለአንድ ወር ብቻ ቆየና አክሬ የቦሊቪያ ግዛት ሆና ቀረች።
ከዚያ በኋላ የአክሬ ሕዝብ አለቃ ወታደሩ ሆዜ ፕላሲዶ ዴ ካስትሮ ሆነ። እሱ የ30,000 ሰዎች አብዮታዊ ሠራዊት አሠለፈ፤ በአክሬ አብዮት (1894 ዓም) ብዙ ውግያዎች ያሸንፍ ነበር። በጥር 1895 ዓም ፕላሲዶ ሦስተኛውን «የአክሬ ሪፐብሊክ» አዋጀ። ከዚሁ ሁናቴ የተነሣ ከአገራት መካከል የሆነ ሁከት ሊሆን መሠለ።
በመጨረሻ በኅዳር 1896 ዓም በተዋዋለው በፔትሮፖሊስ ስምምነት ዘንድ፣ ቦሊቪያ ይግባኝ ማለቱን ለብራዚል ለ፪ ሚሊዮን ፓውንድ በመለዋወጥ ሸጠው። ከዚያ ውል ጀምሮ እስካሁንም ድረስ አክሬ የብራዚል ክፍላገር ሆናለች።