ዲሞክራቲክ ፓርቲ (እንግሊዝኛ: Democratic Party) በአሁኑ ጊዜ ካሉት የአሜሪካ ሁለት (ማለትም ሪፐብሊካንን ጨምሮ) ዋና ዋና ፓርቲዎች አንዱ ነው። ይህ የፖለቲካ ፓርቲ በዓለማችን ረዥሙን እድሜ ካስቆጠሩት ፓርቲዎች አንዱ ሲሆን በአሜሪካም ቢሆን ለረጅም ዘመን ተከታታይ አለመፍረስን ያሳየ ነው። በ2004 እ.አ.አ. 72 ሚሊዮን የሚደርሱ የተመዘገቡ ድምፅ ሰጭዎች ነበሩት።[1] በአሁኑ ጊዜ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የሆኑት ባራክ ኦባማ በፓርቲው ታሪክ የፕሬዝዳንትነትን ማዕረግ ያገኙ 14ኛው ዲሞክራት ሲሆኑ 15ኛው ፕሬዝዳንት ናቸው።