ጊዜ

Melkamu Halgete.G +2511149734861


የዓለማችን የጊዜ ቀጠናወች (ሰዓት ክልል)]] ጊዜ ኩነቶችን (ክስተቶችን) ለመደርደር፣ ቆይታቸውን ለማነጻጻር፣ በመካከላቸውም ያለፈውን ቆይታ ለመወሰን በተረፈም የነገሮችን እንቅስቃሴ መጠን ለመለካት የሚያገለግል ነገር ነው። ጊዜ በፍልስፍናሃይማኖትሳይንስ ውስጥ ብዙ ጥናት የተካሄደበት ጽንሰ ሃሳብ ቢሆንም ቅሉ እስካሁን ድረስ በሁሉ ቦታ ለሁሉ የሚሰራ ትርጓሜ አልተገኘለትም።

የጊዜ መተግበሪያ ትርጉም ለዕለት ተለት ኑሮ ጠቃሚነቱ ስለታመነበት ከዘመናት በፊት ጀምሮ እስካሁን ይሰራበታል። ይህ መተግበሪያ ትርጉም ለምሳሌ ሰከንድን በመተርጎም ይጀምራል። ማለት በቋሚ ድግግሞሽ የሚፈጠሩ ኩነቶችን/ክስተቶችን በማስተዋል የተወሰነ ድግግማቸውን አንድ ሰከንድ ነው ብሎ በማወጅ የመተግበሪያ ትርጉሙ (ለስራ የሚያመች ትርጉሙ) ይነሳል። ለምሳሌ የልብ ተደጋጋሚ ምት፣ የፔንዱለም ውዝዋዜ ወይም ደግሞ የቀኑ መሽቶ-ነግቶ-መምሸት ወዘተ.. እነዚህ ኩነቶች እራሳቸውን በቋሚነት ስለሚደጋግሙ ከነሱ በመነሳት ሰዓትንና ደቂቃን ማወጅ ይቻላል (መሽቶ ሲነጋ 24 ሰዓት ነው፣ ልብ ሲመታ ወይም ፔንዱለም አንድ ጊዜ ሄዶ ሲመለስ አንድ ሰኮንድ ነው፣ ወዘተ..) ። የመተግበሪያ ትርጉሙ ተግባራዊ ጥቅም ይኑረው እንጂ «ጊዜ በራሱ ምንድን ነው?» ፣ ወይም ደግሞ «ጊዜ አለ ወይ?» ወይም ደግሞ «ጊዜ የሚባል ነገር በራሱ አለ ወይ?» ለሚሉት ጥያቄወች መልስ አይሰጥም።

በአሁኑ ወቅት ጊዜ በሁለት አይነት መንገድ ይታያል፦

1. አንደኛው አስተሳሰብ ጊዜ ማለት የውኑ አለም መሰረታዊ ክፍል ሲሆን፣ ማንኛውም ኩነት (event) የሚፈጠርበት ቅጥ ነው።