ጤና ኣዳም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። ጤር አደም
Ruta chalepensis ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያድገውና የታወቀው ጤና ኣዳም ነው። ዶ/ር ፈቃዱ እንደጻፉት ሌላ ዓይነትም ኣለ። ከፈረንጅ ጤና ኣዳም (Ruta graveolens) ጋር እንዳይምታታ መለየት ከሚቻልባቸው ኣንዱ በኣበባዎቹ ነው።
== በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር=ወይናደጋማ ቦታ
በባህላዊ መድሃኒት፣ የጤና አዳም ቅጠል ጭማቂ በቡና ኢንፍሉዌንዛን ለማከም እንደሚረዳ ተዘግቧል።[1]ባህላዊ መድሃኒት ውስጥ ተክሉ እንደ ትኩሳት እና እብጠትላሉ በርካታ ህመሞች እንደ ዕፅዋት መድኃኒትነት ያገለግላል . እንዲሁም የጤና አዳም ቅጠልና ፍሬ ማኘክ ለመጋኛ ወይም ለሆድ ቁርጠት ማስታገሻነት ያገለግላል። ቅጠሉና ፍሬው ከፌጦ ዘር ጋር ሲበላ ለሆድ ቁርጠት መፍትሄ ይሆናል። ከፌጦ ዘርና ከጠጅ ሳር ሥር ጋር ተቀላቅሎ ደግሞ ለሆድ ቁርጠት፣ ወይም ለከብት ጎሎባ ይሠጣል። በተጨማሪም የጤና አዳም ቅጠልና ፍሬ ከጠጅ ሳር ሥር፣ ከነጭ ሽንኩርትና ከኣጣጥ ቅጠል ጋር ተቀላቅሎ ለሆድ ቁርጠት ይበላል።[2] ወይም ቅጠሉ ከነጭ ሽንኩርትና ውሃ ጋር ተቀላቅሎ ብቻ ለሆድ ቁርጠት ይጠጣል።[3]
ጤና አዳም በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እና በአውሮፓ ሲገኝ የተለያዩ ዝርያዎችም አሉት ከነዚህም መካከል በ አውሮፓ እና በሰሜን አፍሪካ ፣ ምስራቅ አፍሪካ ኢትዮፕጲያ የሚገኙት ተጠቃሽና ዋነኞቹ ናቸው። ጤና አዳም በ አበባ የሚራባ የዕጽዋት ዝርያም ጭምር ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |