ጥቁር ኣዝሙድ (Nigella sativa) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
ጥቁር አዝሙድ ቅመሙ ለአያሌ ምክንያት ይጠቀማል፣ ከነዚህም አንዱ የማጣፈጫው ጸባይ ነው። በጥንት ዳቦዎችን ለማጣፈት ብዙ ይጠቀም ነበር። አሁን ግን በተለይ በመጠጥ፣ ከቁንዶ በርበሬ፣ ኮረሪማና ዝንጅብል ጋራ ተቀላቅሎ ይጠቀማል። ብርቱ መጠጦች እንደ አረቄ ወይም ካቲካላ ይህን ጨምረዋል።
ለጥቁር አዝሙድ ጥቅም የተደረጀው ምክንያት የራስ ምታት እና የተለያዩ በሽቶችን ለማባረር ችሎታው እንዳለው በአፍ ይነገራል። ራስ ምታቱን ለማባረር፣ ዘሮቹ፣ ከተቀለጠ ቅቤ ጋር ተቅላቅለው፣ በንጹሕ ጨርቅ ተጠቅልለው፣ ባፍንጫው ይሸተታሉ።[1]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |