ጥቁር እንጨት (Prunus africana) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
ልጡ በአፍሪካዊ ባህሎች ስለሚፈለግ፣ የሚያሳስብ አደጋ ሁኔታ አለው፤ በካሜሩንም ለዚህ ጥቅም ታርሷል።
በሰፊ ከመካከለኛ እስከ ደቡባዊ አፍሪካ ይገኛል።
እንጨቱ ጽኑ ነውና ለሳንቃ ይጠቀማል።
ቅጠሎቹ ለቁስል ፋሻ እንደ ተጠቀሙ ተብሏል።[1]
በልዩ ልዩ አፍሪካዊ አገራት ባህላዊ መድሃኒቶች ውስጥ ረጅም ታሪክ አለው። ልጡ ወይም የልጡ ውጥ ለትኩሳት፣ ወባ፣ ቁስል ፋሻ፣ የፍላጻ መርዝ፣ ሆድ ቁርጠት፣ የሚያስቀምጥ፣ ኩላሊት በሽታ፣ ሞርሟሪ፣ ጨብጡ፣ እና እብደት ተጠቅሟል።.[2] ከዚህም በላይ፣ ያበጠ ፍስ ውሃ እጢ ለማከም እንደሚችል በትንትና ስለ ተረጋገጠ፣ ውጡ በአውሮጳም ይፈለጋልና ይሼጣል። [3]
ገመሬ ጦጣ (ጎሪላ) በኖረበት አገር ፍሬውን ይወድዳል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |