1 አንተፍ

«ሖር ሰኸርታዊ» የሚለው ምልክት፤ በጭላቱ ራስ የ«2ቱ አገራት» ዘውዶች አሉ።

1 አንተፍ ሰኸርታዊ ግብጽን ከጤቤስ (11ኛው ሥርወ መንግሥት) የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ዘውዶቹን ተጭኖ ንጉሣዊ ስም ሰኸርታዊ («ሁለቱን አገራት ጸጥ የሚያደርገው») ነበረው። እንዲያውም ግን ወደ ስሜንም ሆነ ወደ ደቡብ ከጤቤስ የራቁት አገረ ገዦች ወዲያው አምጸው አይገዙለትም ነበር። ከነዚህ መሃል በተለይ የአንቅቲፊ ግዛት በደቡብ ይዘገባል። ከአንቅቲፊ ዕረፍት በኋላ ግን የገዛቸውን ኖሞች (1-3) እንደገና ለጤቤስ ሃያላት እንደ ወደቁ ይመስላል። እንዲሁም ሰኸርታዊ ወደ ስሜን ዘምቶ የግዛቱን ጠረፍ ትንሽ እንዳስፋፋው ይመስላል።

ነብኸፐትሬ (2 መንቱሆተፕ) ከትግል በኋላ ግብጽን በሙሉ ገዝቶ ስለ ነበር፣ አሁን ብዙዎች ሊቃውንት የነብኸፐትሬ ዘመን ከ3ቱ አንተፎች (ሰኸርታዊ፣ ዋሃንኽ እና ናኽት-ነብ-ተፕነፈር) በኋላ መጣ በማለት ይገምታሉ። በዚሁ የጨለማ ዘመን መዝገቦች በቂ ስላልሆኑ ይህ እርግጥኛ አይደለም።

ቀዳሚው
2 መንቱሆተፕ
ግብፅ ፈርዖን ተከታይ
2 አንተፍ