1 ካዳሽማን-ኤንሊል

1 ካዳሽማን-ኤንሊል ከ1383 እስከ 1368 ዓክልበ. ድረስ በካርዱንያሽ (ባቢሎን) ካሳዊ ንጉሥ ነበረ። በአማርና ደብዳቤዎች መካከል 3 ደብዳቤዎች ለግብጽ ፈርዖን ለ3 አመንሖተፕ እንደ ጻፈ ይታወቃል። በ1368 ዓክልበ. 2 ቡርናቡርያሽ ተከተለው።

ከካዳሽማን-ኤንሊል ጀምሮ የካሳውያን ነገሥታት መጠነ ዘመናት ታውቀዋል። ከእርሱ አስቀድሞ የነበረው የካሳውያን ንጉሥ 1 ኩሪጋልዙ ሲሆን፣ የዘመኑን ቁጥር የሚገልጽ ሰነድ ግን እስካሁን አልተገኘም። ስለዚህ ከ1383 ዓክልበ. በፊት በትንሽ 'ጨለማ ዘመን' ባቢሎን ስንት አመት ያሕል በካሳውያን እንደ ተገዛ ለታሪክ ሊቃውንት አጠያያቂ ጉዳይ ሆኗል። (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዩ።)

ቀዳሚው
1 ኩሪጋልዙ
ባቢሎን ንጉሥ (ካሣዊ) ተከታይ
2 ቡርናቡርያሽ