==
መርካውሬ ሶበክሆተፕ | |
---|---|
![]() | |
«መርካውሬ ሶበክሆተፕ» የሚል በአንዱ ሐውልት | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1648-1646 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ሰዋጅካሬ ሆሪ |
ተከታይ | መርኸፐሬ ? |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
መርካውሬ 7 ሶበክሆተፕ በላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት ከ1648 እስከ 1646 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።
ስሙ የታወቀው ከሦስት ምንጮች ነው፦
ከመርካውሬ ሶበክሆተፕ ቀጥሎ እነማን በጤቤስ እንደ ገዙ ግልጽ አይደለም፤ ብዙ ስሞች ከቶሪኖ ቀኖና እንደ ጠፉ ይመስላል። ከሥነ ቅርስ የታወቁት ግን መርኸፐሬ እና ሰኸቀንሬ ብቻ ናቸው። እነዚህ ለረጅም ጊዜ እንደ ገዙ አይታስብም። በዚህም ሰዓት በአቢዶስ ዙሪያ አዲሱ የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት ነጻ እንደ ሆነ ይታስባል። የሚቀጠለው የጤቤስ ፈርዖን ጀሁቲ የ16ኛው ሥርወ መንግሥት ጀማሪ ተብሏል።
በዚሁ ዘመን የሥርወ መንግሥቱ ሥልጣን ከጤቤስ ከተማ በጣም እንዳልራቀ፣ ሂክሶስም ወገኖች በስሜን እንደ ገዙ ይታስባል።
ቀዳሚው ሰዋጅካሬ ሆሪ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1648-1646 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ መርኸፐሬ ? |