The Saint (ዘ ሰይንት) ከ1962 እስከ 1969 እ.ኤ.አ. ድረስ በኢንግላንድ የተሠራ የሰለላ ድራማ ነው።
«ዘ ሰይንት» (ቅዱሱ) ሳይሞን ቴምፕላር ሲሆን እሱ እንደ 20ኛ ክፍለዘመን ሮቢን ሁድ ወይም እንደ ሰላይ የሚስራ የግል ወንጀል መርማሪ ነው። ይፋዊ ድርጅቶች ተበዳዩን ሊረዱት ካልቻሉ ወይም ካልፈለጉ፣ ሳይሞን ቴምፕላር ለራሱ ይረዳዋል፤ ሆኖም «ቅዱሱ» በሚል መጠሪያ ቢባልም፣ ቴምፕላር እራሱ ምንጊዜም ሕጉን የሚጠብቅ አይሆንም። ስለዚህ በፖሊሶቹ አለቃ ተቆጣጣሪ ክሎድ ዩስቴስ ቲል አስተያየት፣ ተምፕላርን እንደ ተራ ወንጀለኛ ይቆጥረዋል፤ ዳሩ ግን ድርጊቶቹ ለበጎው እስኪሆኑ ድረስ፣ አለቃ ተቆጣጣሪ ቲል ይታግሳቸዋል።