Y

የላቲን አልፋቤት
A B C D E F
G H I J K L M
N O P Q R S T
U V W X Y Z
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

Y / yላቲን አልፋቤት 25ኛው ፊደል ነው።

የY መነሻ እንደ ሌሎቹ FUV እና W ሁሉ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ዋው» ደረሰ።

ፊንቄ ጽሕፈት የ«ዋው» ድምጽ እንደ ተናባቢ («ው») ሲሆን፣ በጥንታዊ ግሪክ አልፋቤት ግን ይህ ምልክት የአናባቢ ድምጽ «ኡ»፣ በኋላም «ኢው» (Υ, υ ወይም «ኢውፕሲሎን») ለማመልከት ተጠቀመ።

ኤትሩስክኛ ደግሞ ይህ «Y» ለአነባቢው «ኡ» ይወክል ነበር። በሮማይስጥ ቅርጹ ከ400 ዓም ያህል በኋላ እንደ «V» ተቀየረ፣ ይህም አንድላይ ተነባቢውን «ው» ወይም አናባቢውን «ኡ» አመለከተ።

በኋላ የግሪክኛ ቃላት በሮማይስጥ ፊደል ለመጻፍ፣ /ኢው/ የሚል አናባቢ ጉድለት ለመሞላት የሮሜ ቄሣር ክላውዴዎስ አዲሱን ፊደል ፈጠረ፤ ከክላውዴዎስ ዘመን በኋለ ግን (46 ዓም) የ ጥቅም ተተወ። በ85 ዓም አካባቢ አዲሱ ፊደል «Y» በቀጥታ ከግሪክ ለ፪ኛ ጊዜ ተበደረ።

በሚከተሉ ዘመናት የ«Y» ድምጽ ባብዛኛው ከ/ኢው/ ወደ /ኢ/ ተቀለለ። በዘመናዊ እንግሊዝኛ አጠራር ይህ ደግሞ ስለ ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ «Y» እንደ /አይ/ ሊያሰማ ይችላል፤ ለምሳሌ፦ my /ማይ/ (የኔ) ። በተጨማሪ እንደ ተናባቢው /ይ/ ይጠቅማል፤ ይህ የነባሩ የመካከለኛ እንግሊዝኛ ፊደል «ȝ» (/ይ/፣ /ኅ/ ወይም /ግ/) በመተካት ነው።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Y የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።