ሀቫና (እስፓንኛ፦ La Habana /ላ አባና/) የኩባ ዋና ከተማ ነው። በ1507 ዓ.ም. በእስፓንያውያን በደሴቱ ደቡብ ዳርቻ ተመሠርቶ ከተማው በዚህ ሥፍራ ግን አልተከናወነም። ስለዚህ በ1511 ዓ.ም. መሠረቱ በስሜን ዳርቻ ወዳለ ሥፍራ ተዛወረ።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 2,686,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 2,343,700 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 23°07′ ሰሜን ኬክሮስ እና 82°25′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |