ሂለሪ ሮድሃም ክሊንተን የ42ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ የፕ/ቢል ክሊንተን ባለቤትና የኒውዮርክ ግዛት ሰናተር ናቸው። ሚስ ክሊንተን በ2008 እ.ኤ.አ. የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ቅድመ ምርጫ ተወዳድረው በሌላኛው ዴሞክራቲክ ተመራጭ ባለጋራቸው ተሸንፈው ወጥተዋል። ይሁን እንጂ ከ17 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ስለመረጣቸው በአሜሪካ ቅድመ ምርጫ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ሕዝብ ብዛት ተብሎላቸዋል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |