ሄፐታይቲስ ኤ | |
---|---|
Classification and external resources | |
![]() A case of jaundice caused by hepatitis A | |
ICD-10 | B15 |
ICD-9 | 070.0, 070.1 |
DiseasesDB | 5757 |
MedlinePlus | 000278 |
eMedicine | med/991 መለጠፊያ:EMedicine2 |
Patient UK | ሄፐታይቲስ ኤ |
MeSH | D006506 |
ሄፐታይቲስ ኤ (በመደበኛነትተላላፊ ሄፐታይተስ ) በሚል የሚታወቀው አጣዳፊ ተላላፊ በሽታ የሚያጠቃውም ጉበት ሲሆን ሄፐታይተስ ኤ በሚባል ቫይረስ (HAV)አማካይነት ይተላለፋል። [1] በርከት ባሉ የበሽታው ክስተቶች በተለይም በታዳጊዎች ዘንድ የሚታየው የህመም ምልክት ብዙውን ጊዜ አነስ ያለ ነው ወይም ምንም ምልክት አይታይም። [2] በበሽታው በተያዙ ሰዎች ላይ ምልክቶቹ የሚታዩ ከሆነ ሊታዩ የሚችሉበት ጊዜ በሁለትና ስድስት ሳምንታት መካከል ነው። [3] የህመም ምልክቶቹ ሲኖሩ ለስምንት ሳምንታት ያህል የሚቆዩ ሲሆኑ እነዚህም፦ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ ተቅማጥ፣ የቆዳ ቀለም ብጫ መሆን, ትኩሳት, እና የሆድ ህመምን የሚያካትት ነው። [2] ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች በበሽታው ከተያዙበት ጊዜ አንስቶ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተደጋጋሚ የሆነ የህመም ምልክቶቹን ያያሉ። [2] አጣዳፊ የጉበት ስራ ማቆም ችግር አልፎ አልፎ ሲከሰት በአረጋዊያን ዘንድ ግን ክስተቱ የተለመደ ነው። [2]
ብዙውን ጊዜ በሽታው የሚሰራጨው ቫይረሱ ባለበት አይነምድር የተበከለ ምግብ ወይም ውሃ በመብላትና በመጠጣት ነው። [2] [[ሼልፊሽ/የባህር ዓሳ]ን በደንብ ሳይበስል ከተመገቡት እሱም አንዱ የበሽታው ምንጭ ነው። [4] እንዲሁም በበሽታው በተያዘ ሰው ጋር በሚኖር የቅርብ ግንኙነት/ንኪኪ ሊተላለፍ ይችላል። [2] ምንም የህመም ምልክት የማይታይባቸው ህፃናትም ቢሆኑ በሽታውን ወደ ሌሎች ማስተላለፍ ይችላሉ። [2] አንድ ሰው አንዴ በበሽታው ተይዞ ከዳነ ዕድሜ ልኩን ተመልሶ አይያዝም /እንደ ክትባት ያገለግለዋል። [5] የህመም ምልክቱ ከሌሎች በርካታ በሽታዎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ በሽታውን ለማወቅ በሚደረግ ምርመራ የደም ናሙና ወስዶ ማየት ያስፈልጋል። [2] ይህ ከሚታወቁት አምስት ሄፐታይቲስ ቫይረስ: ኤ, ቢ, ሲ, ዲ, and ኢ መካከል አንዱ ነው።
የ ሄፐታይቲስ ኤ ክትባት በሽታውን ለመከላከል ውጤታማ ነው። [2][6] አንዳንድ አገሮች ለህፃናት በተከታታይ ሲሰጡ በህፃንነታቸው ላልተከተቡና በበሽታው የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ሆኖ ለተገኘ አዋቂዎችም ክትባቱ እንዲሰጣቸው ያደርጋሉ። [2][7] ክትባቱ ለዕድሜ ልክ ያገለግላል። [2] ሌሎች የመከላከያ ዘዴዎች [እጅን መታጠብ]] እና ምግብ በደንብ ማብሰልን ያጠቃልላል። [2] ምንም የተለየ ህክምናም የለውም፤ ለ ማቅለሽለሽ ወይም ተቅማጥ እረፍትና መድሃኒት እንዳስፈላጊነቱ ሊታዘዝ ይችላል። [2] በሽታው ብዙውን ጊዜ ያለ ቀጣይ የጉበት ህመም ሙሉ በሙሉ ይድናል። [2] አጣዳፊ የጉበት ስራ ማቆም ችግር ከተከሰተ፤ ህክምናው ጉበት የመቀየርዘዴን መጠቀም ያስፈልጋል። [2]
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከሚታይባቸው ምልክቶች በመነሳት ምርመራ ሲደረግላቸው በሽታው የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ይሆናል። [2] ባጠቃላይ አስር ሚሊዮኖች ይያዛሉ ተብሎ ይገመታል። [8] የበሽታው ክስተት በብዛት የሚታወቀው ዝቅተኛ የግልና የአካባቢ ንጽና ባለበትና በቂ ንፁህ ውሃ በሌለው የዓለም ክፍል ነው። [7] በበማደግ ላይ ባለው ዓለም 90 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት በ10 ዓመት ዕድሜያቸው በበሽታው ስለሚያዙ አዋቂዎች በሚሆኑበት ጊዜ መልሰው አይያዙም። [7] ህፃናት በልጅነታቸው ጊዜ ለበሽታው ባማይጋለጡባቸው ባደጉት አገሮች ለአዋቂዎች በቂ ክትባት በማይኖርበት ወቅት በሽታው በወረርሽኝ መልክ ይከሰታል። [7] በ 2010, አጣዳፊ የሄፐታይቲስ ኤ በሽታ 102,000 ሰዎችን ለህልፈት ደርጓል። [9] የዓለም ሄፐታይቲስ ቀን በየዓመቱ ጁላይ 28 ስለ ቫይራል ሄፐታይቲስግንዛቤ ለመፍጠር ይከበራል። [7]