==
ሆተፒብሬ | |
---|---|
በኤብላ የተገኘው የሆተፒብሬ ዱላ | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1806-1803 ዓክልበ. |
ቀዳሚ | አመኒ ቀማው |
ተከታይ | ዩፍኒ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
አባት | አመኒ ቀማው? |
==
ሆተፒብሬ ቀማው ሲሃርነጅሀሪተፍ (ወይም ሰሀተፒብሬ) ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1806 እስከ 1803 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የአመኒ ቀማው ተከታይ ነበረ። ሕልውና ከአንዳንድ ቅርስ ተረጋግጧል። ከነዚህ በተለይ የሚጠቀሰው በኤብላ የተገኘ ዱላ ቅርስ ነው፤ ይህ በኤብላ ገዥ ኢመያ መቃብር በመገኘቱ የሆተፒብሬም ስም ስላለበት ከፈርዖኑ ለኢመያ የተሰጠ ስጦታ እንደ ነበር ይገመታል።
የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት እንደሚያስረዳው የአመኒ ቀማው ልጅና ተከታይ ይሆናል። ስያሜው «ቀማው ሲሀርነጅሀሪተፍ» ማለት «የቀማው ልጅ ሲሀርነጅሀሪተፍ» ይመስለዋል።
በራይሆልት አስተሳሰብ፣ የሆተፒብሬ ተከታይ ዩፍኒ ሲሆን ይህ ምናልባት ወንድሙ ወይም አጎቱ ይሆናል።
ቀዳሚው አመኒ ቀማው |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን | ተከታይ ዩፍኒ |