ላብራዶር ሪትሪቨር | |||||||||||||||||||||||||
ሌላ ስሞች | ላብራዶር | ||||||||||||||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
ቅጽል ስሞች | ላብ | ||||||||||||||||||||||||
መነሻ ሃገር | ካናዳ | ||||||||||||||||||||||||
| |||||||||||||||||||||||||
| |||||||||||||||||||||||||
ውሻ (Canis lupus familiaris) |
ላብራዶር ሪትሪቨር ተብለው የሚታወቁት ውሻዎች ላብራዶር እንዲሁም ላብ በሚሉትም ስሞች ይጠራሉ። እነኝህ ውሻዎች ሪትሪቨር (የታደኑ እንስሳትን ወደ አዳኙ የሚያመጡ) ከሚባለዉ ዝርያ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው። በባህሪያቸው የተለሳለሱ ሲሆኑ ከህጻናት እና ከአዛውንቶች ጋራ በጥሩ ሁነታ ይግባባሉ። ላብራዶሮች ስፖርት ወዳድና ተጫዋች ሲሆኑ በብዙ የውሻ ባለቤቶች ዘንድ ተመራጭ ናቸው።
በብዙ ሃገሮች የእርዳታ ዉሻን ሚና ይሚጫወቱት እነዚህ ውሻዎች በተለይም አይነ-ስውራንን እና ከኦቲዝም ጋራ የሚኖሩ ሰዎችን እንዲሁም የህግ አስከባሪ ባለሙያዎችን እንዲያግዙ ማሰልጠን ይቻላል።
ሰውነታቸው ከትላልቆች ተርታ የሚመደበው እነዚህ ውሻዎች በብዛት ክብደታቸው ለወንዶች ከ29-36ኪግ ለሴቶች ድግሞ ከ25-32ኪግ ድረስ ይመዝናል።
ለላብራዶሮች ተቀባይ ተብለው የተመዘገቡት ቀለሞች ጥቁር፥ ቢጫ (ከሽሮ እስከ ቀላ ያለ ቀበሮ) እና ቡናማ ግራጫ (ከመካከለኛ እስከ ጥቁር ቡኒ) ናቸው።