- ግማሽ ኪሎ ግራም ቤት የተዘጋጀ ወይም ታሽጐ የሚሸጥ ላዛኛ
- 5 ትልልቅ እንቁላል
- 5 መካከለኛ ጭልፋ ቦሎኔዝ ሶስ
- 8 የሾርባ ማንኪያ (200 ግራም) የገበታ ቅቤ
- 5 መካከለኛ ጭልፋ ቢሻሜል ሶስ
- 1 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተፈጨ ቺዝ
- 1. ጨው፣ ዘይትና በርከት ያለ ውሃ አፍልቶ ላዛኛውን እየዘረጉ መጨመር፣
- 2. ለአምስት ደቂቃ ካበሰሉ በኋላ እንዳይሰባበር ወይም እንዳይቦካ በጥንቃቄ አውጥቶ ቀዝቃዛ ውሃ ያለበት ሰፋ ያለ ዕቃ ውስጥ መጨመር፣
- 3. እንዳይሰባበር ተጠንቅቆ አውጥቶ በንፁህ አቡጀዲ ላይ አድርጐ ጫን፣ ጫን እያደረጉ መጠጥ እንዲል ማድረግ፤
- 4. የዳቦ መጋገሪያ ትሪ ላይ ሁለት የሾርባ ማንኪያ ቅቤ መቀባት፤
- 5. ትሪው ላይ ላዛኛውን በነጠላው ከዳር እስከዳር ማንጠፍ፤
- 6. የሥጋ ሶሱንና እንቁላሉን ደባልቆ መምታት፤
- 7. ከውሁዱ 2 መካከለኛ ጭልፋ አውጥቶ የተነጠፈው ላዛኛ ላይ በተመጣጠነ መልኩ መቀባት፤
- 8. ሁለት መካከለኛ ጭልፋ ቢሻሜል ሶስ ከላዩ ጨምሮ ማዳረስ፤
- 9. በዚህ ዓይነት አንድ ተጨማሪ ድርብ መጨመር፤
- 10. ከላዩ ላዛኛ በማንጠፍ ከዳር እስከ ዳር መሸፈን፣
- 11. መጀመሪያ ቀሪውን ውሁድ፣ ቀጥሎም የቀረውን ቢሻሜል ጨምሮ መቀባት፤
- 12. ቺዙን ከዳር እስከዳር መነስነስና ቅቤ አልፎ፣ አልፎ ጣል ጣል ማድረግ፤
13. ወርቃማ መልክ እስከሚያወጣ ፉርኖ ቤት ወይም የዳቦ መጋገሪያ ውስጥ ማብሰል።
[ከዚህ በተለየ መጀመሪያ ቢሻሜል ሶሱን፣ ቦሎኔዝ ሶሱንና እንቁላሉን አዋህዶ በየደረጃው ውህዱን ከላይ በተጠቀሰው መልኩ በመቀባት ማዘጋጀት ይቻላል።]