የከባቢያችን አየር በነጎድጓድ በታጀበ ብርቅርቅታ ውስጡ ያዘለውን ኮረንቲ ወደ ምድር ሲወረውረው መብረቅ እንለዋለን። መብረቅ ብዙን ጊዜ ከዝናብ ጋር ተያይዞ ይምጣ እንጂ ከእሳተ ጎሞራ ወይም ደግሞ ከአውሎንፋስ ጫፍ ላይ ተፈናጥቆ ወደምድር የመምዘግዘግ ባህርይም ያሳያል። ከከባቢው አየር በሚነሳው ኮረንቲ የሚወድቀው መብረቅ፣ ጫፉ እስክ 60ሺህ ሜትር በአንድ ሰከንድ ውስጥ መሄድ ይችላል፣ ሙቀቱ ደግሞ እስከ 30 ሺህ ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያደርሳል። ከዚህ ሙቀቱ የተነሳ በአሸዋ ላይ ቢወድቅ አሸዋውን በማቅለጥ ፉልገራይት ወደሚባለው የመስታውት አይነት በቅጽበት ይቀይረዋል።
በነገራችን ላይ በአመት እስከ 16 ሚሊዮን ጊዜ መሬትን መብረቅ ይመታታል።