?መተሬ | ||||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||||
| ||||||||||||||
''Glinus lotoides'' L. |
መተሬ (ሮማይስጥ፦ Glinus lotoides) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። የኮሶ መድኃኒት ነው።
በኢትዮጵያ፣ በተለይ በቆላ ወንዝ ደለሎች ለምሳሌ በዋቤ ሸበሌ ወንዝ ባለው ከላፎ ደለል ይገኛል።
የኮሶ ትል ለማስወጣት በሰፊ ይጠቀማል፣ በገበያም ይሸጣል።[1]
በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ በተደረገ ጥናት መሠረት፣ ትሉን ለማስወጣት፣ ቅጠሉ ወይስ ዘሩ ተደቅቆ በውሃ ይጠጣል። ይህም ከብሳና ልጥ ጋር ሊጠጣ ይችላል። ዘሮቹም ደግሞ ከኑግ ዘር ጋር በለጥፍ ይበላል።[2][3]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |