መቱ

መቱ
መቱ ከተማ

መቱ በደቡብ-ምዕራብ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የንግድ ከተሞች መካከል አንዷ ስትሆን በኦሮሚያ ክልልኢሉባቦር ዞን ዋና ከተማ ነች። ከሶር ወንዝ አጠገብ የምትገኘው ይህች ከተማ 8 ° 18′N 160 35 ° ላቲትዩድና ሎንጊትዩድ እንዲሁም 1605 ሜትር ከፍታ አላት። መቱ አዲሱ ህገ-መንግስት እስከ ፀደቀበት ጊዜ ድረስ ከ1978 ዓ/ም በፊት የቀድሞው ኢሉባቦር ክፍለ አገር ዋና ከተማ ነበረች ። መቱ ከ1930ዎቹ ጀምሮ የቡና ንግድ ዋና ገበያ ስለሆነች ከአካባቢው አርሶአደሮች ሰብሉን ለመግዛት በከተማዋ በርካታ የውጭ ዜጎች ይኖራሉ ። ከዚያው ጊዜ ጀምሮ ከተማዋ ከጎሬ እና አዲስ አበባ ጋር በስልክ የተገናኘች ነች። የከተማዋ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ በአቅራቢያው የሚገኘው የሶር ወንዝ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ነው ።