ማይክሮሶፍት

Microsoft Corp. www.microsoft.com
ኢንዱስትሪ ኮምፒዩተር ሶፍትዌር
ኮምፒዩተር ሐርድዌር
ቴሌቪዥን
ምርምርና ማዳበር
ኢንተርኔት
ዓይነት የሕዝብ
የምስረታ_ቦታ አልበከርኪኒው ሜክሲኮ (April 4,1975 እ.ኤ.አ.)
ዋና_መሥሪያ_ቤት ሬድመንድዋሽንግተንአሜሪካ
ቁልፍ_ሰዎች ቢል ጌትስ፥ መሥራችና ዳይሬክተር
ፖል አለን፥ መሥራች
ምርቶች ዊንድዎስ
ኦፊስ
ሰርቨርስ
ስካይፕ
ቪዥዋል እስቲድዮ
ዳይናሚክስ
አዡር
ኤክስ ቦክስ
ሰርፌስ
ገቢ $44.28 ቢሊዮን (2006 እ.ኤ.አ.)
የተጣራ_ገቢ $44.28 ቢሊዮን (2006 እ.ኤ.አ.)
የሰራተኞች_ብዛት 114,000 (በሰኔ 30 2016 እ.ኤ.አ.)


ማይክሮሶፍት ኮርፖሬሽን ዓለም-አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው። እንደ ጁላይ 2006 እ.ኤ.አ. ማይክሮሶፍት 71,553 ሠራተኞች በ102 ሀገሮች ሲኖረው፣ ዓመታዊ ገቢው 44.28 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ነው። እጅግ በጣም ብዙ የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ማምረትና ማዳበር ዋና ዓላማው ነው። ዋና መስሪያቤቱ በሬድመንድ፣ ዋሽንግተንአሜሪካ የሚገኝ ሲሆን፣ ታዋቂ ምርቶቹ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ስርአተ ክወና እና ማይክርሶፍት ኦፊስ ግሴት ሶፍትዌር ያጠቃልላሉ። ከሶፍትዌሮች ሌላ፥ ኤም.ኤስ.ኤን.ቢ.ሲ የኬብል ቴሌቪዥን፥ ኤም.ኤስ.ኤን. ዌብሳይትማይክሮሶፍት ኢንካርታ የኢንተርኔት መዝገበ ዕውቀት፥ የቤት መዝናኛ እና ሌሎችም ምርቶችና አገልግሎቶችን ያቀርባል።