ሥነ ፈለክ (አስትሮኖሚ) ከመሬት ከባቢ አየር ውጪ የሚገኙ ክስተቶችን የሚያጠና የሳይንስ ክፍል ነው። ቃሉ አስትሮኖሚ ከግሪክ የመጣ ሲሆን የፀሐይ የከዋክብትና የጨረቃዎች ሕግ ማለት ነው።
ሥነ ፈለክ ከጥንታዊ ሳይንሶች አንዱ ነው።
== በአስትሮኖሚ ውስጥ የሚገኙ ንዑስ ክፍሎች፦
- አስትሮሜትሪ - በሰማይ የሚገኙ ነገሮችን ቦታ እና አንቅስቃሴ የሚያጠና ክፍል።
- አስትሮፊዚክስ - ከመሬት ውጪ የሚገኙ ነገሮች ተፈጥሮ ሕግጋት ጥናት (ፊዚክስ)።
- ኮስሞሎጂ - የዓለም አጀማመርና ለውጥ ጥናት።
- ስቴላር አስትሮኖሚ - የከዋክብትና የጨረቃዎች ጥናት።
- አስትሮባዮሎጂ - የዓለም የሕይወት ጥናት።
የሥርዓተ ፀሓይ ፕላኔቶች (ፈለኮች)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]