ሬይኪያቪክ

ሬይክያቪክ (Reykjavík /ረይጫቪክ/) የአይስላንድ ዋና ከተማ ነው።

ሬይክያቪክ

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 200,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 118,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 64°08′ ሰሜን ኬክሮስ እና 21°56′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ከተማው በ862 ዓ.ም. ላንድናማቦክ የሚባለው መጽሐፍ እንደሚገልጸው በቫይኪንግ መሪ በኢንጎልፉር አርናርሶን ተመሠረተ።