ሳንቶ ዶሚንጎ የዶሚኒካን ሪፑብሊክ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 2,851,300 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 2,252,400 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 18°30′ ሰሜን ኬክሮስ እና 69°57′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
እስፓንያውያን ከተማውን በ1486 ዓ.ም. በመሠረታቸው ከአዲሱ አለም ከሁሉ የቆየው አውሮፓዊ ከተማ ሆኗል ማለት ነው።
ከ1928 ዓ.ም. እስከ 1953 ዓ.ም. የከተማው ስም ሲዩዳድ ትሩሒዮ ይባል ነበር። ከዚያ ስሙ ወደ 'ሳንቶ ዶሚንጎ' ተመለሠ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |