ሻውካንግ

ሻውካንግ (ቻይንኛ፦ 少康) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ዘመን ንጉሥ ነበር።

በ1946 ዓክልበ. ግድም አባቱ ሥያንግ በአመጸኞቹ ሃን ዥዎና ልጁ ጅያው ተገደለ፤ ንግሥቷ ሚን እርጉዝ ሆና አመለጠችና በሚከተለው ዓመት በስደት ሻውካንግን ወለደች።

እርሱ አድጎ ሻውካንግና ቢትዎደዱ ሜ ከ1926 እስከ 1906 ዓክልበ. ድረስ አመጸኖቹን ተዋጉ። በመጨረሻ በ1906 ዓክልበ. በአንዪ በሆነ ውግያ ሃን ዥዎና ልጁ ጅያው ተገደሉ፣ ሻውካንግም ንጉሥ ሆኖ የቻይና መንግሥት ያንጊዜ አልጠፋም።

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ በመጀመርያው ዓመት መሳፍንቱ ወደ ግቢው መጥተው ተገዙለት፤ በሚከተለውም ዓመት የፋንግ አሕዛብ መጥተው ተገዙለት። በ፫ኛው ዓመት የእርሻ ሚኒስትር ወደ ሹመቱ መለሰው። በ፲፩ኛው ዓመት ሚኒስትሩን የሻንግ መስፍን ሚንግ ቢጫ ወንዝን እንዲያስቆጣጠር አዘዘው። በ፲፰ኛው ዓመት ጊቢውን ወደ ይወን አዛወረው። በ፳፩ኛው ዓመት፣ ዓረፈና ልጁ ተከተለው።

ቀዳሚው
ሃን ዥዎ (የአመጽ አለቃ)
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ ተከታይ