ቀንጠፋ ወይም ቆንጥር (Pterolobium stellatum) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
ሌላ ዝርያ፣ የግራር ዛፍ አይነት Acacia brevispica ደግሞ «ቀንጠፋ» ተብሏል።
ሁለቱም በአተር አስተኔ ወይም «አባዝርት» አስተኔ ናቸው።
በምሥራቅ አፍሪካና በየመን ይገኛል። በድንጋያማ ዳገት፣ በወንዝ ደለል፣ በጫካ ዳርቻ ይገኛል።
ለቊጥቋጦ-ኣጥር ይስማማል። ቡቃያዎቹም ለከብት መኖ ይሰበሰባሉ።
በኢትዮጵያ፣ የተደቀቀው ልጥ ጭማቂ በቆዳ ፋቂ ለማቀላት ተጠቅሟል።[1] ቅጠሎቹም ሲደቀቁ ጨለማ-ቀይ ቀለም ይሠራል።
ትኩስ ቅጠሎቹ ለመድሃኒት ይኘካል፣ ለምሳሌ የሳምባ ነቀርሳን ወይም ተመሳሳይ የመተንፈስ ችግሮችን ለማከም።[2]
የቀንጠፋው ፍሬ ለማስታወክ እንደሚጠቀም ተዘግቧል።[3]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |