ቀዓት (ዕብራይስጥ፦ /ቀሃት/፤ ግሪክኛ፦ /ካዓጥ/) በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የሌዊ ልጅ፣ የእንበረም አባትና የሙሴ አያት ነበር።
በኦሪት ዘጸአት ፮፡፲፰ ዘንድ፣ የቀዓት ሌሎች ልጆች ይስዓር፣ ኬብሮን እና ዑዝኤል ተባሉ፤ የቀዓትም እድሜ 133 ዓመታት ደረሰ። በኦሪት ዘኊልቊ ምዕራፍ ፫ እና ፬ እንደሚለን፣ የቀዓት ትውልድ ወይም ቀዓታውያን ከሌዋውያን መካከል አንዱ ወገን ናቸው፤ የዚህም ወገን ኃላፊነት ታቦትና ቅዱስ ንዋይ ነው።
በመጽሐፈ ኩፋሌ ፳፬፡፳፮ የሌዊ ሚስት ስም ሜልካ፣ «ከቃራ (ወይም በሌሎቹ ቅጂዎች ታራ) ልጆች ወገን ከሚሆን ከአራም ልጆች የተወለደች»፣ ይህችም የቀዓት እናት ነበረች። ኩፋሌ ፴፩፡፲፩ ቀዓት ከሌዊ ልጆች ጋር ወደ ግብፅ ከገቡት ሰዎች መካከል ይዘረዝራል።
በተጨማሪ «የሌዊ ምስክር» የተባለው ጽሑፍ (ከ፲፪ቱ አበው ምስክሮች አንዱ) እንዲህ ይላል፦