ቀይ | |
---|---|
ሞገድ | 700–635 nm |
ድግግሞሽ | 430–480 THz |
ቀይ የቀለም አይነት ሲሆን የሞገድ ርዝመቱ ከ 700–635 nm እና የድግግሞሽ መጠኑ ከ 430–480 THz ነው።
ቀይ ቀለም፡ በብርሃን ዉስጥ፤ አእማድ ወይም ብርሃንን ከሚምሰርቱት የመሰረት ቀለም አንዱ ነው። እንዲሁም በፒግሜንት ቀለም ዉስጥ ዐእማድ ቀለም ነው።ዐእማድ ማለት መሰረት ማለት ነው፡ በእንግሊዘኛው primary colors ይባላል። ሁለት አይነት ዓእማድ ቀለሞች አሉ፡ አንዱ የፒግሜንት ዐእማድእ ቀለም ውይም የሰአሊዎች ዐእማድ ቀለም ሲሆን፤ ሌላኛው ደሞ የብርኃን ዐእማደ ቀለም ነው፡፡
የፒግሜንት ቀለም ከሶስት መስረታዊ ቀለም የተዎጣጣ ነው፡ ዝርዝሩ እነሆ፡ ቀይ....ቢጫ....ስማያዊ:፡ የብርሃን ዐእማደ ቀለም ደሞ እንደሚከተለው ነው። ቀይ..አረንጓዴ...ስማይዊ። ወደ ቀይ እንመለስ ቀይ የሞገድ ርዝመቱን እላይ የዊኬፒድያ አዘጋጆች አስቀምጠዉታል ይመልከቱ። ቀይ ባጠቃላይ በፍካቱ ጸለምት ከሚባሉት ቀለም ዉስጥ ይመደባል፡ እንድ ቢጫ የፈካ ብሩህ አይደለም፡፡ የቀለም ብርሁነት ፍካት ራሱን የቻለ አርስት ነው። ቀይ ቀለም ከሌላ ዐእማድ ቀለም ጋር ሲደባለቅ እንዲሁም ሲቀጥን የሚዎልዳቸው አስተኔ nuanc ቀልሞች አሉ። ለአብነት ይኸው፡ ቀጋ-ቀይ kadmiumRed..የጽጌረዳ-ደም..ALizarinKarmesin ....ብርቱካኔ- ቀይ orange-Red ውይም ጯሂት-ቀይ፡ የተባለው እጂግ ደማቅ ቀይ ስለሆነ ነው፡ ባጭሩ ውይም በተለምዶ ደማቅ -ቀይ ውይም ብሩህ ቀይ ተብሎ ሊጠራ ይቺላል። ሃመር -ቀይ pink-Red ጠይም ቀይ..Medium red ..ጸለምት -ቀይ... bordo.ቪኖ-ቀይ..ውይም ቀይ -ስርቀይ...እሳቱ-ተሰማ ቀይ
እሳቱ ተሰማ በ1950- 1970 እ. አ. አ. አቆጣጠር የክቡር ዘበኛ ድምጻዊ ሙዚቀኛ፤ አባል ነበር ፡ ከዘፈኑ ዉስጥ የሚታወቀው የአበሻ ወይዛዝርቶች የሚስማማቸው ያገራቸዉን ጥበብ ሲለብሱ ነው በሚል አርስት ስር ይዜመው ዘፈን ነው፡፡ ይህን ዘፈን ሲያዜም ሁሌ ቀይ ጥለት ያለው ያገር ልብስ ለብሶ ነበር። በዚህ የተከበረ ምክንይት አንስቶ 1960 እ.አ.አ ቀይ ነጠላ ሞድ ህኖ ይለበስ ነበር። የጥለቱም ስም እሳቱ ተሰማ ይባል ነበር፡፡ ይህ ቀይ ቀለም ጃኖ. ቀይ መባል ይቺላል፡ ጃኖ ለበአል ግቢ ንጉስ እጅ ሲነስ ጃኖ ነጠላ ተለብሶ ነው የክብር ነጠላ ማለት ነው፡ ቀለሙ ቀይ ብቻ ነው መሆን ያለበት፡ የነጠላዉም ርዝመት አሰራር ከተለመደው ነጠላ ይለያል እንዲሁም ልቃቂቱ የተለየ ነው።