ቀዳማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ በዙፋን ስማቸው ወልደ አምበሳ እ.ኤ.አ ከ1413-1416 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ናቸው። የቀዳማዊ ዓፄ ዳዊትና የንግስት ጺዮን መንገሻ ልጅ ነበሩ፡፡ ታሪክ አጥኝው ዋሊስ በድጅ ቀዳማዊ ቴወድሮስ ለ3ዓመት [1] ነገሡ ቢልም በብዙ ታሪክ አጥኝወች ዘንድ ለ9 ወር ብቻ እንደነገሡ ይታመናል። ምንም እንኳ የነገሡበት ዘመን አጭር ቢሆንም የኒህ ንጉሥ ዘመን በጥንቱ የኢትዮጵያውያን ትዝታ ውስጥ ምንጊዜም የማይረሳና እጅግ ተወዳጅ ነበር። በ18ኛው ክፍለ ዘመን ጎንደር ተጉዞ የነበረው የስኮትላንዱ ጄምስ ብሩስ እንዲህ ሲል ይዘግባል፦
«በኒህ ንጉሥ ዘመን የተሰራ አንድ ድንቅ ነገር መኖር አለበት ምክንያቱም የአገዛዝ ዘመናቸው እጅግ አጭር ቢሆንም፣ ከሁሉ በፊት የኒህ ንጉሥ ዘመን በኢትዮጵያውያን ዘንድ የተወደደ ነው። እንዴውም ብዙወች የሚያምኑት ንጉሡ ከሞቱበት እንደገና ተነስተው አበሻን ለአንድ ሺህ አመታት እንደሚገዙ ነው። በዚህ መጭው አገዛዛቸው ሁሉም ጦርነት ያበቃል፣ ደስታ፣ መትረፍረፍና ሰላም ለሁሉም ይዳረሳል።» |
— ጄምስ ብሩስ[2] |
ቀዳማዊ ቴወድሮስ "ሃይማኖተኛና የሃይማኖት ድርሳናትን በጣም እሚወዱ" እንደነበር ዋሊስ በድጅ የተሰኘው የታሪክ አጥኝ ስንክሳሩን በመተርጎም አስቀምጧል። በኋላ ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ እንደፈጸሙት የቤተክርስቲያናንን መሬት ለገበሬው አክፋፍለዋል። ይህም አጼይኩኖ አምላክ ለቤተክርስቲያን ይገባል ያሉትን 1/3ኛ የአገሪቱን መሬት ስምምነት የጣሰ ነበር። [3] እኒሁ ንጉስ ወደ እየሩሳሌም ለመጓዝ ፈልገው አቡነ ማርቆስ ለደህንነታቸው በመስጋት እንዳይሄዱ አድርገዋል።
ምንም እንኳ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ ለገበሬወች ቢያከፋፍሉም እኒሁ ንጉስ በኋላ ላይ በተዋህዶ ቤተከርስቲያን ቅዱሳን ተርታ ተመደቡ። ለዚህም ምንክንያታቸው ሃይማኖተኝነተቸው፣ ለድሆች የነበራቸው ሩህሩህነትና በጊዜው እንግዳ የነበረው በአንድ ሚስት መወሰናቸው ነበር።
ቴዎድሮስ ከአዋሽ ወንዝ ማዶ እንደሞቱ በመዋዕላቸው የተፃፈ ሲሆን የታሪክ ፀሀፊው ታደሰ ታምራት ግን በውጊያ የመጣ ሞታቸውን ለመደበቅ እንደተሞከረ ይገምታል። "[4] አጼ በእደ ማርያም ከተቀበሩበት ተድባባ ማርያም አፅማቸውን አስውጥተው በአጥሮንሳ ማርያም ቤተክርስቲያን፣ መርሐ ቤቴ እንዲያርፍ አድርገዋል[5]።
ከቴዎድሮስ ማለፍ ቀጥሎ ታናሽ ወንድማቸው ዓፄ ይስሐቅ ዙፋን ላይ ወጡ።
|
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |