ቅርንፉድ

ቅርንፉድ

ቅርንፉድ (Syzygium aromaticum) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ዛፍ ተክል ነው።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ተክሉ ሁሌ ለም ዛፍ ነው፣ እስከ 8-12 ሜትር ድረስ ይቆማል፣ ታላላቅ ቅጠሎችና በጫፉ ላይ ክፍት ቀይ ኅብረ-አበቦች አሉት። አበቦቹ አረንጓዴ ሆነው ሲጀምሩ፣ በምርት ጊዜ ክፍት ቀይ ይሆናሉ። የአበባው አቃፊዎች ለቅመም የሚመረቱ ናቸው።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቅርንፉድ ዛፍ መጀመርያ መናኸሪያ እስከ 1760 ዓም ድረስ የማሉኩ ደሴቶች ኢንዶኔዥያ ብቻ ነበር። ሆኖም ከነዚህ ደሴቶች የቅርንፉድ ንግድ እስከ ሶርያ በ1730 ዓክልበ. እንደ ደረሰ በሥነ ቅርስ ታውቋል። በ1760 ዓም ግድም አንድ የፈረንሳይ ዜጋ ፒዬር ፗቭር የዛፉን ቡቃያ ሰርቆ በዛንዚባር እንዳስተከለው ይባላል፤ ይህም የደሴቶቹን ምኖፖል አስጨረሰው። አሁንም በተለይ እንደ ሰብለ ገበያባንግላዴሽ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ሕንድማዳጋስካርፓኪስታንስሪ ላንካታንዛኒያ ይታረሳል።

የተክሉ ጥቅም

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ለሳል እና ጉንፋን በሽታዎች፡፡

  • አፋችን ንጹህና ጥሩ ማዕዛ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡
  • ማቅለሽለሽን ያስታግሳል/ያስቆማል፡፡
  • በጨጓራ ችግር/ህመም ወቅት ይረዳናል፡፡
  • የሆድ መነፋትን ያስታግሳል፡፡
  • የአፍ ቁስለትን ይቀንሳል፡፡
  • የጥርስ ህመምን እና የድድ መድማትን ያስታግሳል፡፡
  • ከፍተኛ የኮሌስትሮልን መጠን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡
  • የደም ዝውውርን ይጨምራል፡፡
  • ጀርምና ጐጂ ባክቴሪያዎችን የሚገድል ንጥረ-ነገር ይዟል፡፡