በስነ አምክንዮ "በቂ" እና "አስፈላጊ" የሚሉት ቃላቶች በጣም የጠራ ትጓሜና አጠቃቀም አላቸው።
መጀመሪያ ምሳሌዎችን እንይ፡
P የተባለ አረፍተ ነገር (ድንጋጌ) Q ለተባለ ድንጋጌ እውነት መሆን አስፈላጊ ነው ከተባለ በግልባጭ ሲተረጎም "P እውነት እንዲሆን የግዴታ Q እውነት መሆን አለበት ," ወይም " P ውሸት ከሆነ Q ም ውሸት ነው" እንደማለት ይቆጠራል። ለምሳሌ ማየት በQ ቢወከልና አይን በP ቢወከል፣ P ለመሆን Q አስፈላጊ ነው። Q ከሆነ (ከታየ)፣ P እውነት ነው ማለት ነው (አይን አለ)።
ይህ ጉዳይ በሂሳብ ጥናት በቀላሉ እንደዚህ ይጻፋል፡ (Q => P), ትርጉሙም P የ"Q " መዘዝ ነው ማለት ነው። ወይም በሌላ አነጋገር Q እውን ሲሆን Pን ያመላክታል ማለት ነው። ምሳሌ፡ እይታ => አይን መኖር ፤ እይታ መፈጠሩ አይን መኖርን ያመላክታል። ወይም ደግሞ አይን መኖር የእይታ መዘዝ ነው።
ምሳሌዎች፡
P የተባለ አረፍተ ነገር Q የተባለ አረፍተ ነገር እውነት እንዲሆን በቂ ፣ ነው ካልን P እውነት መሆኑ ብቻ Qን እውነት ያደርገዋል። በሌላ ጎን P ውሸት ቢሆን Q ውሸት ነው ለማለት በቂ ማስረጃ የለንም። በሌላ አነገጋገር " P ከሆነ Q" ወይም ደግሞ "P => Q," በሚል ሲያጥር፣ " የP መሆን Qን ያመላክታል" ማለት ነው። ከዚህ አንጻር Q የP መዘዝ ነው ማለት ነው።
በሂሳብ ጥናት "በቂ" እና "አስፈላጊ" የተገላቢጦሽ ግንኙነት አላቸው። ለQ፣ P አስፈላጊ ከሆነ፣ ለP፣ Q በቂ ነው ማለት ነው። ምሳሌ፡ ድመት ለመሆን እንስሳ መሆን አስፈላጊ ሲሆን፣ በአንጻሩ እንስሳ ለመሆን ድመት መሆን በቂ ነው።
P ፣ ለ Q በቂና አስፈላጊ ነው ካልን ትርጉሙ "P ከሆነ Q እንዲሁም Q ከሆነ P" ወይም ባጭሩ "P ከሆነና ከሆነ ብቻ Q" እንደማለት ነው። በሂሳብ ሲጻፍ P <=> Q ማለት ነው። P ና Q በዚህ ወቅት ምንም ልዩነት የላቸውም፣ አንድ ናቸው ማለት ይቻላል።
ምሳሌዎች: