Republika y'u Burundi |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: ቡሩንዲ ብዋኩ (የኛ ብሩንዲ) Burundi Bwacu |
||||||
ቡሩንዲ በቀይ ቀለም
|
||||||
ዋና ከተማ | ጊቴጋ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ኪሩንዲ ፈረንሣይኛ |
|||||
መንግሥት {{{ፕሬዚዳንት |
ፒዬር ንኩሩንዚዛ |
|||||
ዋና ቀናት የነጻነት ቀን |
ሰኔ 24 ቀን 1954 (July 1, 1962 እ.ኤ.አ.) |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
27,834 (142ኛ) 10 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት የ2008 እ.ኤ.አ. ቆጠራ |
11,178,921 (86ኛ) 8,053,574 |
|||||
ገንዘብ | የቡሩንዲ ፍራንክ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +2 | |||||
የስልክ መግቢያ | +257 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .bi |
የቡሪንዲ ሪፕብሊከ (ቀድሞ ኡሩንዲ (urundi) የተባለ ሲሆን) በአፍሪካ ውስጥ የምትግኝ ተንሽ አገር ናት። በሩዋንዳ፥ ታንዛኒያ፥ እና በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ትዋሰናልች።
አገሯ ወደብ-የለሽ ብትሆንም ከታንጋንዪካ ሐይቅ ጋር ትዋሰናለች። የቡሩንዲ ዋና ከተማ እስከ ታህሳስ 2011 ዓም ድረስ ቡጁምቡራ ሲሆን ከዚያ ወደ ጊቴጋ ተዛወረ። የሀገሩ የህዝብ ብዛት ወደ 8.7 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል።
የቱዋ፣ ቱትሲና ሁቱ ብሔሮች በቡሩንዲ ለአምስት ምእተ ዓመታት ያህል ኖረዋል። የቱትሲ ሕዝብ ቡሩንዲን በየንጉሥ መንግሥትነት ለሁለት መቶ ዓመታት ያህል መርቷል። ግን በ፳ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ፣ አካባቢው በጀርመንና ቤልጅግ ቁጥጥር ስር ላይ ኖሯል። ቡሩንዲና ሩዋንዳም አንድ ላይ ሩዋንዳ ኡሩንዲ እየተባሉ በቅኝ ግዛት ጊዜ ተጠርተዋል።
በአካባቢው የሰፈነው የፖለቲካ ቀውስ በቡሩንዲ የእርስ በርስ ጦርነት ፈጥሮአል። በአሁኑ ጊዜ ቡሩንዲ ፕሬዝዳንታዊ የተወካዮች ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሆና ትመራለች። ከሀገሩ ሕዝብ ውስጥ ፷፪ ከመቶ የሮማ ካቶሊክ እምነት ተከታይና ከ፰ እስከ ፱ ከመቶ እስላም ሲሆን የተቀረው ሌሎች የክርስትና ዕምነቶችን ወይም ባህላዊ ሃይማኖቶችን ይከተላል።
ቡሩንዲ ከዓለም አስር እጅግ ድሀ ሀገራት አንዷ ናት። የዚህ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ ጦርነቶች፣ ሙስና፣ የትምህርት አለመስፋፋትና የኤድስ በሽታ ይጠቀሳሉ። የተፈጥሮ ሀብቶቿ መዳብና ኮባልትን ይጨምራሉ። ኤክስፖርት ከምታደርጋቸው ምርቶች መካከል ዋናዎቹ ቡናና ስኳር ናቸው።
የመጀመሪያው የቡሩንዲ ነዋሪዎች የፒግሚ ሰዎች ናቸው። ከዛም በባንቱ ሕዝቦች ባብዛኛው ተተክተዋል። በ16ኛው ክፍለ ዘመን ነጻ መንግሥት ነበረ። ከዛ በ1903 እ.ኤ.አ. የጀርመን ቅኝ ግዛት ሆነች። በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ወደ ቤልጅግ ተላለፈች።
|