ባንጊ

ባንጊ (Bangui) የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 810,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 669,800 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 04°23′ ሰሜን ኬክሮስ እና 18°37′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ከተማው በፈረንሳዮችኡባንጊ ወንዝ ላይ በ1881 ዓ.ም. ተመሠረተ።