ቤተ መጽሀፍት የተለያዩ መረጃዎች፣ ጥራዞች፣ መጽሀፎች፣ እለታዊ እትሞች እንዲሁም ሌሎች ማጣቀሻዎች በዓይነት በዓይነት ተደርድረው የሚገኙበት ቤት ነው። ይህ ስብስብ በመንግሥት፣ በተቋማት ወይም በግለሠብ ደረጃ ሊቋቋም ይችላል።