ብሩክ ጋብሪኤል ሊጀርትዉድ (ላቲን፡ Brooke Gabrielle Ligertwood) (የተወለዱት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 15 ቀን 1983 ነው) በመድረክ ስማቸው ብሩክ ፍሬዘር በተሻለ ይታወቃሉ፣ ኒውዚላንዳዊ የወንጌል ዘማሪ እና የዜማ ደራሲ ሲሆኑ 2010 በተለቀቀው ነጠላ ዘማቸው ማለትም “ሰምትንግ ኢን ዘ ዌተር” በደምብ ይታወቃሉ። ፍሬዘር ከ ዉድ + ቦን ጋር የመቅረጫ ውል ከመፈራረማቸው በፊት ዋት ቱ ዱ ዊዝ ደይላይት (2003) እና አልበርታይን (2006) የተሰኙ ሁለት የስቱዲዮ አልበሞችን በኮሎምቢያ ሪከርድስ አውጥቶ ነበር። ሦስተኛው የስቱዲዮ አልበም ፍላግስ፣ እ.ኤ.አ. በ 2010 የተለቀቀ ሲሆን እስከዛሬም በጣም ስኬታማ አልበማቸው ነው። በጣም የቅርብ ጊዜው አልበማቸው፣ ብሩታል ሮማንቲክ በህዳር 2014 በቫግራንት ሪከርድስ ተለቋል።[1]
ፍሬዘር እ.ኤ.አ. ከ 2005 እስከ 2010 የአውስትራሊያ ክርስቲያናዊ የሙዚቃ ቡድን የሆነውን የሂልሰንግ ዎርሺፕ አባል ሆኑ፤ በጋቢቻ ስማችው ማለትም በብሩክ ሊጀርትዉድ ለተመዘገበው “ዋት ኤ ቢዩትፉል ኔም” የተሰኘ እና ለግራሚ አሸናፊነት ያበቃቸውን መዝሙር ደራሲ እና መሪ ድምፃዊ ከነበሩበት እ.ኤ.አ. 2016 ጀምሮ እንደገና ቡድኑን ተቀላቅለዋል።[2] “ዩ ሰይ ዐይ ኤም” እና “ዐዌክ ማይ ሶል” ጭምሮ በፍሬዘር የተፃፉ ብዙ ታዋቂ መዝሙሮች አሉ።