ብሳና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
ዛፉ ባብዛኛው ከ7 እስከ 15 ሜትር ይደርሳል።
በኢትዮጵያ በጣም ተራ ነው።
ፍሬዎቹና የሥሮቹ መረቅ ለአባለዘር በሽቶች ተጠቅመዋል።
የተደቀቀው ልጥ ከኮሶ ወይም መተሬ ጋር ተቅላቅሎ ትልን ያስወጣል።
ዘሮቹና ሙጫዎቹ መርዛም ናቸው፣ ለአሣ መርዝ ይጠቀማሉ።
የቅጠሎቹ ውጥ ለአናት እከክ ይጠቀማል።
ለወፍ በሽታ፦ የብሳና ቡቃያ ቅጠል መረቅ ከሰንሰል ጋር ተቀላቅሎ፣ ቁንዶ በርበሬና ቅቤ ይጨምር ለ፫ ቀን በዳቦ ይበላል፤ በርካታ ወተትም ይጠጣል እንጂ ሥጋ ወይም ዘይታም ምግቦች መተው አለበት።[1]
ከልዩ ልዩ ቦታዎች ባህላዊ መድሃኒት ውስጥ፣ የብሳና ላፒስ እንደ ቅባት ለችፌ፣ ቋቁቻ ወይም ጭርት ያከማል። እንዲሁም የብሳና ዛፍ ልጥ ዱቄት ለቁስሎች ይለጠፋል። የአገዳው ልጥ ዱቄት በወተት ለልብ ድካም ይጠጣል።[2]
የብሳና፣ የጨጎጊትና የክትክታ ቅጠላቅጠል ተደቅቀው እንደ ለጥፍ ደግሞ ለቁስል ይለጠፋል።
ለትኩሳት («ምች»)፣ የብሳና ቅጠልና የቀበሪቾ ሥር እንደ ጢስ ይናፈሳል። የብሳና ቅጠል ከተለያዩ ሌሎች አይነት ቅጠሎች ጋር በውሃ ተፈልቶ እንፋሎቱ ለ«ምች» ይናፈሳል፦ ለምሳሌ ነጭ ባሕር ዛፍ፣ ዳማ ከሴ፣ ዋንዛ፣ ጥንጁት ቅጠል፣ ፌጦ ዘር።
ለውሻ በሽታ፦ የብሳና ልጥ፣ የእምቧይ፣ የገበር እምቧይና የግንዶሽ ሥር፣ የጽድ ቅጠልና የጤፍ ዘር፣ አንድላይ ተጋግሮ ተድቅቆ በውሃ ይጠጣ። እንዲሁም ለእንስሳ ውሻ በሽታ፣ በትንሽ ጤፍ እንጀራ ይበላ።[3]
በዘጌ ልሳነ ምድር ጥናት እንደ ተዘገበ፣ ለቁርባ ማከም የብሳና ቅጠል ወደ ወጥ ይጨመራል። የቅጠሉም ዱቄት ለተቅማጥ ይጠጣል፣ ለወፍ በሽታ ደግሞ ለ፯ ቀን ይጠጣል።[4]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |