ቮላፒውክ

ዮሐን ማርቲን ሽላየር
የቮላፒውክ ሎጎ

ቮላፒውክ (Volapük) ሰው ሠራሽ ቋንቋ ነው። የተፈጠረው በ1872 ዓ.ም. ሮማ ካቶሊክ ቄስ በሆነው በዮሐን ማርቲን ሽላየርባደን ጀርመን ነበር። ሽላየር አንድ ዓለም አቀፍ ቋንቋ እንዲፈጥር እግዚአብሐር በሕልም እንዳዘዘው አመነ። ከዚያ በኋላ የቮላፒውክ ጉባኤ በጀርመን አገር በ1876 እና በ1879 ተደርጎ እንደገና ጉባኤ በፓሪስ ፈረንሳይ1881 ይፈጸም ነበር። በዛ ጊዜ 283 ክለቦች 25 መጽሔቶችና 316 መጻሕፍት ስለ ቮላፒውክ ነበሩ።

የቮላፒውክ ቃላት የተለቀሙ በብዛት ከእንግሊዝኛ ሲሆን አንዳንድ ቃላት ደግሞ ከፈረንሳይኛ እና ከጀርመንኛ ተወሰዱ። ነገር ግን ቃሎቹ በጣም ተቀየሩ። ለምሳሌ 'ቮላፒውክ' የሚለው ስም የተለቀመው ከእንግሊዝኛ ቃላት world /ወርልድ/ (ዓለም) እና speak /ስፒክ/ (ንግግር) ሆኖ /ወርልድ/ ወደ vol ቮል፤ /ስፒክ/ ወደ pük /ፒውክ/ ተቀየረ። ስዋሰው ደግሞ እንደ አውሮጳ ቋንቋዎች ስዋሰው ይመስላል።

ምሳሌ፦

vol ቮል - ዓለም
vols ቮልስ - ዓለሞች
vola ቮላ - የዓለም
volas ቮላስ - የዓለሞች
vole ቮሌ - ለዓለም
voles ቮሌስ - ለዓለሞች
voli ቮሊ - ዓለምን (ተሳቢ)
volis ቮሊስ - ዓለሞችን

ይህ ቋንቋ ለጥቂት ጊዜ ዘበናይ ሆኖ ቀረ። ነገር ግን በ1879 ሌላ ሰው ሰራሽ ቋንቋ ኤስፔራንቶ ስለ ተፈጠረ የቮላፒውክ ተነጋሪዎች ቁጥር እጅግ ተቀነሰ። በ1923 ዓ.ም. ሰዋሰው ታደሰ፤ ዳሩ ግን በአዶልፍ ሂትለር ዘመን ደግሞ በጀርመን ስለ ተከለከለ ቋንቋው ከዚያ በኋላ ሊከናውን አልቻለም። ዛሬ በዓለም ላይ ከ 20 እስከ 30 ሰዎች ይችሉታል።

አባታችን ሆይ ጸሎት፦

O Fat obas, kel binol in süls, paisaludomöz nem ola!
Kömomöd monargän ola!
Jenomöz vil olik, äs in sül, i su tal!
Bodi obsik vädeliki govolös obes adelo!
E pardolös obes debis obsik,
äs id obs aipardobs debeles obas.
E no obis nindukolös in tendadi;
sod aidalivolös obis de bas.
Jenosöd!

አጠራሩ፦

ኦ ፋት ኦባስ፥ ኬል ቢኖል ኢን ሲውልስ፥ ፓይሳሉዶሙዝ ኔም ኦላ!
ኩሞሙድ ሞናርገን ኦላ!
ዤኖሙዝ ቪል ኦሊክ፥ ኧስ ኢን ሲውል፥ ኢ ሱ ታል!
ቦዲ ኦብሲክ ቨዴሊኪ ጎቮሉስ ኦቤስ አዴሎ!
ኤ ፓርዶሉስ ኦበስ ዴቢስ ኦብሲክ፥
ኧስ ኢድ ኦብስ አይፓርዶብስ ዴቤሌስ ኦባስ።
ኤ ኖ ኦቢስ ኒኑኮሉስ ኢን ቴንዳዲ፤
ሶድ አይዳሊቮሉስ ኦቢስ ዴ ባስ።
ዤኖሱድ!
Wikipedia
Wikipedia
ቮላፒውክ ውክፔዲያ አለ!