ተልባ (Linum usitatissimum) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
በኢትዮጵያ ወይም በየትም አገር ተልባ ስለ ዘሩ ይታረሳል።
ባጠቃላይ የሚያለዝብ የሚያስቀምጥ መጠጥ ሆኖ ይጠቀማል። ከሁዳዴ ጾም በኋላ ለፋሲካ ድግስ ለማዘጋጀት የሚያለዝብ ተልባ መጠጥ ይጠጣል። መጠጡም ለመስራት፣ ዘሮቹ ትንሽ ይጠበሱና ይፈጩ።
የቀቀለ ዘሩ መዳን ለማፋጠን በቁስል ላይ ይደረጋል። ይህ ዘዴ ደግሞ ጥይት ከቁስል ለማውጣት እንደሚረዳ ተጽፏል።[1]
የተልባ ወጥ ይሠራል። ከዘሩ ምግብ በላይ ስለ ዘይቱ እና ስለ ጭረቱ (ተልባ እግር) ይታረሳል። ተልባን መብላት ኮሌስትሮልን ከደም ለማጥራት፣ የደም ግፊትንም ለማሳነስ እንደሚችል በዘመናዊ ሳይንስ ታውቋል።
የደረቀ ተልባ ዘር መረቅ በስኳር ለትቅማጥ መስጠቱ ተዘግቧል።[2]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |