ቻርልተን ሄስተን (እ.አ.አ. ከኦክቶበር 4፣ 1923 እስከ ኤይፕሪል 5፣ 2008) አሜሪካዊ የፊልም፣ የቲያትር እና የቴሌቪዥን ተዋናይ ነበር። ቻርልተን የሚታወቀው በተለያዩ ጊዜያት በሰራባቸው እና በተሳተፈባቸው ፊልሞች ነው። ለምሳሌ እንደ ሙሴ (Moses) ሆኖ The Ten Commandments በተባለው ፊልሙ ላይ፣ በተጨማሪም ኮለኔል ጆርጅ ቴይለር (Colonel George Taylor) ሆኖ በPlanet of the Apes ፊልም ላይ፣ ሮድሪጎ ዲያዝ ዲ ቭኢቫር (Rodrigo Díaz de Vivar) ሆኖ በEl Cid ፊልም ላይ እና ጁዳ ቤን ሁር (Judah Ben-Hur) ሆኖ በBen-Hur ፊልም ላይ መሳተፉ ለታዋቂነቱ ግንባርቀደም ስራዎቹ ናቸው።