ኋሥያ

ኋሥያ (ቻይንኛ፦ 華夏 (ልማዳዊ አጻጻፍ) ወይም 华夏 (የተቀለለ አጻጻፍ) የቻይና ብሔር ሥልጣኔ ወይም ቅድማያቶች የሚወክል ስያሜ ነው። በቻይና ልማዳዊ ታሪክ በባንጯን ውግያ (ምናልባት 2265 ዓክልበ.) የኋንግ ዲ («ብጫው ንጉሥ») ወገን ወይም ዮውሥዮንግያንዲ («የነበልባል ንጉሥ») ወገን ወይም ሸንኖንግ ላይ ድል አደረገ። ከዚህ ድል በኋላ ሁለቱ ወገኖች በኋንግ ዲ ሥር ተባብረው አንድላይ «ኋሥያ» የተባለ ብሔር በቢጫው ወንዝ አካባቢ ፈጠሩ። ይህም ኋሥያ ነገድ የዛሬው ቻይናዊ ዘር አባቶች ነበሩ።