ኋይ

ኋይ (ቻይንኛ፦ 槐) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ዘመን ንጉሥ ነበር። ሌላ ስሙ ፈን (芬) ነው።

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ ለዘመኑ የተዘገቡት ድርጊቶች እንዲህ ናቸው፦ በ1869 ዓክልበ. ግድም አባቱ ዓርፎ ኋይ ተከተለው። በ2ኛው ዓመት «፱ የምሥራቅ ነገዶች» መጥተው አገለገሉት። በ፲፮ኛው ዓመት፣ የልዎ መኮንን ዩንግ ከሆ መኮንን ፈንግ-ዪ ጋር ተዋጋ። በኋይ ፴፫ኛው ዓመት የኩንዉ ገዥ ልጅ ወደ ዮውሱ ገዥነት ሾመው። በ፴፮ናው ዓመት አንድ ክብ ቅርጽ ያለ ወህኒ ቦታ ፈጠረ።

በ፵፬ኛው ዓመት ዓረፈና ልጁ ማንግ ተከተለው።

ቀዳሚው
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ ተከታይ
ማንግ