የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቀድሞው የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
ዶ/ር ነጋሶ ከ1987 እስከ 1994 ዓም ጀምሮ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ዶ/ር ነጋሶ በወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ ባለመስማማታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ከለቀቁ በኋላም በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ በግል ዕጩነት የሕዝብ ድምጽ በማግኘት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆንም አገልግለዋል፡፡
ከመጀመሪያ ባለቤታቸው ደሲቱ ቀጀላ ሁለት ልጆችን ወልደዋል፡፡
በትምህርት እድል ከጀርመን ጎተህ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪአቸውን ያገኙት ዶ/ር ነጋሶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የታሪክ መምህር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
በጀርመን ሃገርም ረጊና አበልት የተባሉ ጀርመናዊት ነርስ እና አዋላጅ ጋር ትዳር በመመስረት አንድ ልጅ ወልደዋል፡፡
የመድረክ መስራች እና በኋላም የአንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባል ሆነውም ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ከዛም ከፖለቲካው ዓለም ራሳቸውን በማግለል የተለያዩ ጥናታዊ ፅሑፎችን በመስራት ሲያቀርቡም ቆይተዋል፡፡
፩ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት | |
ከነሐሴ ፲፮ ቀን ፲፱፻፹፯ እስከ መስከረም ፳፰ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. | |
ምክትል ፕሬዝዳንት | መለስ ዜናዊ |
---|---|
ተከታይ | ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ |
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ከደምቢ ዶሎ | |
ከ2005 እ.ኤ.አ. ጀምሮ | |
የኢትዮጵያ ሽግግር መንግሥት ማስታወቂያ ሚኒስትር | |
የተወለዱት | ደምቢ ዶሎ፣ ኢትዮጵያ |
የፖለቲካ ፓርቲ | ኢህአዴግ (እስከ ሰኔ ፲፭ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ.ም.) አንድነት (ከኅዳር ፳፻፪[1] እስከ ጥር ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. [2]) |
ዜግነት | ኢትዮጵያዊ |
ባለቤት | ሬጂና አቤልት |
Cite error: <ref>
tags exist for a group named "https://aszebheretobia.blogspot.com/2019/04/blog-post_27.html", but no corresponding <references group="https://aszebheretobia.blogspot.com/2019/04/blog-post_27.html"/>
tag was found