ነፍስ የአንድ ሰው ምንነት ማለት ሲሆን በብዙ ሃይማኖቶች ዘንድ ይህ ምንነት አንድ ሰው ከሞተ በኋላ እንኳ የማይጠፋ ነው። ስለሆነም ነፍስ ከአዕምሮ ጋር በብዙ ፍልስፍናዎችና ሃይማኖቶች ዘንድ የተቆራኙ ናቸው። ነፍስና መንፈስ በተለምዶ አንድ ተደርገው ቢታዩም ሁለቱ ይለያያሉ። ነፍስ፣ የአንድ ሰው ምንነት እንደመሆኑ መጠን የራሱ የሆነ መለያ ጠባዮች አሉት ስለሆነም ከሌሎች ነፍሶች ጋር አንድ ላይ ሆኖ ሊቀናጅ አይችልም። መንፈስ ባንጻሩ (ለምሳሌ መንፈስ ቅዱስ) አለም አቀፍ እንደመሆኑ መጠን ብዙ ነፍሶች የሚጋሩት ነው።
ነፍስ ከ«እኔነት» ጋር ምንም ልዩነት የለውም። አንድ ሰው «እኔ ህልው ነኝ» ወይም «በርግጥ እኔ አለሁ» ሲል «እኔ» የሚለው ቃል የሰውየውን ነፍስ ያጠቅሳል። አንድ ሰው ህልው መሆኑን ማረጋገጥ የሚችለው ለነፍሱ ብቻና ለነፍሱ ብቻ ስለሆነ ሰውነቱ የነፍሱ ንብረት እንጂ ነፍሱ እራሱ አይደለም። ይህ አስተሳሰብ ቀልበኝነት የሚባል ፍልስፍና አካል ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |