ነፕቲዩን

ነፕቲዩን፡ (ምልክት፦♆) መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት 8ኛ ( ስምንተኛ ) ነው። ከበፊቱ ኣጣርድቬነስመሬትማርስጁፒተርሳተርን እና ኡራኑስ የተባሉ ፕላኔቶች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ትንሹ ፕሉቶ ይገኛል።

ይህ ፕላኔት በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፕላኔቶች በግዝፈቱ የአራተኛነትን ደረጃ ይይዛል። ግዙፍ የ ጋዝ ክምችት እንደሆነ ይታመናል። በ ረጨቱ ውስጥ የጋዝ ክምችት የሆኑት ፕላኔቶች ጁፒተርኡራኑስሳተርን እና ራሱ ነፕቲዩን ናቸው። በዚህም የተነሳ ጆቪያን ወይም ጁፒተርን መሳይ እየተባለ ይጠራል። በአብዛሃኛው ሃይድሮጅን እና ሂሊየም ከተባሉ ንጥረነገሮች የተሰራ ነው።